Ethio Tribune

Plural News and Analysis on Ethiopia and HOA

 • RSS google news

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS Capital

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS Unknown Feed

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS Unknown Feed

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS Walta

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS DireTube Video

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • Enter your email address to receive notifications of new posts

  Join 481 other followers

 • Meta

 • Articles

 • ምስለ መለስ፡ የማንነቱ ገፅታ

  ምስለ መለስ፡ የማንነቱ ገፅታ

 • Live streaming

 • ETV live streaming
 • RSS Sudan Tribune

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS East Africa News

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS BBC News

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS Aljazeera

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS Climate Change News

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS Technology News

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • Archives

 • Flickr Photos: Ethiopia

Ethio Books World

ስብሃት ገብረእግዚአብሄር
ቅዳሜ ዞሮ ሲመጣ አንዳንድ ጊዜ ከስብሃት ጋር ደብረዘይት እንሄድ ነበር። አንድ ጊዜ እንዲሁ ባቦጋያ ሃይቅ ዳርቻ ከአንድ ወዳጃችን ግቢ ውስጥ እንደ ስጋጃ ከሚለሰልሰው የሳር መስክ ላይ ጋደም ብለን የሃይቁን የማእበል ድምፅ እያዳመጥን ዋልን። ሴት ልጁ ዜና አብራን ነበረች፣

“ለምንድነው ልጅህን ዜና ያልካት ጋሽ ስብሃት?”
“ለምን ነበር መሰለህ? አንዲት በጣም ቆንጆ፣ ስታወራ የምትጥም፣ የምወዳት ዜና የምትባል ሴት ነበረች። እሷን ለማስታወስ በሚል ልጄን ዜና አልኳት…”

ሌላ ቀን ደግሞ አንድ ግሮሰሪ ውስጥ ቁጭ ብለን እየቀማመስን ሳለ በወቅቱ ምስጢር የነበረ አንድ ወሬ ነገርኩት፣
“ህወሃት ችግር ውስጥ እየገባ ነው…”
“ምን ሆኑ?”
“ለሁለት ተከፍለዋል። በሚቀጥለው ሳምንት ይፋ ሊሆን ይችላል”
ስብሃት ብዙ ጊዜ ወዲያውኑ መልስ ይሰጣል። በዚህ ቀን ግን በፀጥታ ጥቂት አሰበና እንዲህ አለኝ፣

“ቢከፋፈሉ መጥፎ አይደለም። አንዱ ሌላውን ለመብለጥ ሲል በመካከሉ ጥሩ አሳብ ሊያመጡ ይችላሉ። አብዮተኞች መከፋፈል ማይቀር እጣቸው ነው። በቻይናና በኩባ ታይቶአል። ካስትሮና ቼ ይለያያሉ ተብሎ የሚታሰብ አልነበረም…”

በዚያን እለት ከደብረዘይት እንደተመለስን ጎተራ አካባቢ መኪና ውስጥ ቁጭ ብለን ብዙ አመሸን። ስብሃት ደረቅ አረቄ ስለሚጠጣ ፈጥኖ ሞቅ ይለዋል። እና ያን ቀን በመካከሉ ብቻውን መሳቅ ጀመረ። ልክ እንደተኮረኮረ ሰው ነበር የሚስቀው። ከመሳቁ ብዛት እንባው ከአይኑ ወረደ። እንዲህ የሚስቀው አንድ ቀልድ ብልጭ ሲልለት ነው።

“ምንድነው እንዲህ ያሳቀህ ጋሽ ስብሃት?”
“የኦብሎሞቭ አገልጋይ ትዝ ብሎኝ ነው” አለ።

በዚያን ጊዜ ኢቫን ጋንቻሮቭ የተባለው የወርቃማው ዘመን ደራሲ ‘ኦብሎሞቭ’ በሚል ርእስ የፃፈውን መፅሃፍ አላነበብኩም ነበር። ስብሃት ምን ትዝ እንዳለው እንዲህ ሲል አጫወተኝ፣

“…ሽማግሌው የኦብሎሞቭ አገልጋይ በጣም ሰነፍ ነበር። ኦብሎሞብ ከስራ ሲመለስ ቤቱ አልተፀዳም፣ አልጋውም አልተነጠፈም፣
‘ለምንድነው አልጋውን ያላነጠፍከው?’ ይለዋል።
‘ጌታ ኢሊያ ኢሊይች… ባነጥፈውም እኮ መልሶ መበላሸቱ አይቀርም። ብጠርገውም ቤቱ መልሶ ይቆሽሻል..’…”
እንደገና ሲስቅ ከቆየ በሁዋላ እንዲህ አለ፣

“ይኸው እየጠጣን ነው። ከዚያም እንሸናለን። እንደገና ደግሞ እንጠጣለን። መልሰን ደግሞ እንሸናለን። እየጠጣን እየሸናን … እየጠጣና እየሸናን እስከመቼ? …”

በርግጥ በስነፅሁፍ እና በታሪክ ዙሪያ ከስብሃት ጋር ማውራት በፍፁም አይጠገብም። በተለይም ኮሚክ እና እንግዳ ጠባይ ያላቸውን ገፀባህርያት አይረሳቸውም። ስብሃት በራሱ ሙሉ ቤተመፃህፍት ነበር። በቀላሉ የመኖር ችሎታው በጣም ይመስጠኝ ነበር። ማንንም ለመምሰል የማይሞክር፣ እራሱን የሆነ እና የልቡን ሁሉ እንዳፈቀደው የሚናገር ሰው በመሆኑ እቀናበት ነበር። ህይወትን በመሰለው መንገድ ኖሮባታል። አምላክ ነፍሱን በገነት ያኑር።

(ተስፋዬ ገብረአብ)

******
ዓይንና ጆሮ መሆን ደስ ይለኛል!
-ስብሐት ገብረእግዚአብሔር
******

******

“[ኒው ዮርክ ከተማ፣ ማንሐታን] … በፓርክ አውራ ጎዳና ላይ ወደ ሚገኘው የፓተርሰን ቢሮ ታክሲ ተከራይታ ሄደች። በመስታወትና በክሮም ከተዋበው ረጅም ህንፃ ደርሳ ከታክሲው ስትወርድ ሆዷን ባር ባር አለው። ወደ ህንፃውም ለመግባት አመነታች። … የተሸከሟት እግሮቿ ሊከዷት ቢቃረቡም እንደምንም ከህንፃው ውስጥ ገብታ ወደ ሊፍቱ አመራች። እንደ ጥይት የሚወረወረው ሊፍትም ሳታውቀው ከሰላሳ ስምንተኛው ፎቅ ደርሶ ቆመ። ሂላሪ እንደዚያ ያለ ህንፃ አይታ አታውቅም። እርግጥ አባቷና እናቷ ለሽርሽር ወደ አውሮፓ ወስደዋቸው በነበረበት ወቅት በሮምና በፓሪስ ከተማ አንዳንድ የሚያስደንቁ ህንፃዎች አይታ እንደነበረ ታስታውሳለች። በተለይ የሮማን ኮሎስየም፣ የፓሪሱን የኢፈል ታወር አትረሳቸውም። ፓሪስ ውስጥ በከረሙባቸው ቀናት ያደሩበት የሪትዝ ሆቴል፣ እናቷ ሶላንጅ እጇን ይዛት በትላልቅ ሱቆች ውስጥ ያደረጉት ጉብኝት አይዘነጋትም። ከሁሉም ከሁሉም ደግሞ አባቷ እናቷን በገደለበት ምሽት እርሱ ምን ብሎ እንደተናገረና እርሷም ምን ብላ እንደመለሰችለትና በንዴትም ዘሎ አንገቷን እንዳነቀው ከህሊናዋ የማይፋቅ ነው።

-ብርቅርቅታ | በዳኒኤላ ስቲል | ተርጓሚ ዓቢይ ደምሴ | ገጽ 110
******
******

ወይ’ዛ ነውራም ጉዳም — ሽመይ ተባሂለ

ይነብር ኣለኹ — ብሰብ ተኾኒነ
እስኪ መልሱለይ — እንታይ’የ በዲለ
አፍቂረ እምበር — መዓስ ነውሪ ገይረ
ሰባት ኢሎምኒ — ዓይኒ ጤል ዝበልዐት
ሰዓበቶ ከኣ — ሕዚ’ውን ሓለፈት
እንተ ኣነ — ወይከ ዘይመስለኒ
ሰባት — ዝበሉ ይበሉኒ
ጥራሕ ይስመረለይ — ፍቕሩ ይቕናዓኒ
ንሱ ናተይ ይኹን — ምስኡ የንብረኒ
ሰብ ኣይከውንን — ካብኡ ኣይትፍለዩኒ
ፀልዩለይ ደኣ — ምሕረት ክወርደኒ
ይሳቐ ኣለኩ — ፍቕሩ በርቲዑኒ።“

-ላህመት | ብ ፋና ገብረ መድህን ተስፋይን አበባ ስዩም ተስፋይን | ገፅ 9

******

******

“….ክንዱ ትከሻዋን፥ ቀኝ እጁ ቀኝ እጇን፥ ትኩስ ትንፋሹ ጆሮዋን፥ አንገትዋን ሲነካት፥ ልዩ ሙቀት፥ የወንድነቱ ሙቀት፥ በዚህ ሁሉ በኩል፥ እንደ ኤሌክትሪክ ማዕበል በሰራካላትዋ ጎርፎ አጋላት። ያ ለምለም፥ ያ ውብ አካላትዋ ከማር ሰፈፍ እንደ ተሰራ ሁሉ፥ ሙቀት እንደሚፈራ ሁሉ፥ ትንሽ በትንሽ መቅለጥ፥ ትንሽ በትንሽ መፍሰስ ጀመረ። ሰውነቷን መግዛት፥ በሰውነቷ ማዘዝ ተሳናት። ወዲያው ሳታስበው፥ ሳታዝዘው፥ ራስዋ ቀና፥ ፊቷ ወደ ፊቱ ዘወር አለና፥ አፏ ተከፍቶ የሱን አፍ ፍለጋ ሲሄድ በመንገድ ተገናኙ። ከዚያ እጆቿ አንገቱን፥ የሱም እጆች የሷን ተጠምጥመው ይዘው፥ አፏ ባፉ፥ አፉ ባፏ ውስጥ ቀለጡ። እሱ በሷ፥ እሷ በሱ ውስጥ ጠፉ። […] ወደ ሌላ ዓለም፥ ወዳንድ አዲስ ዓለም ገቡ።

ትንሽ ዝም ብለው፥ ዓይን ላይን ተያዩና፥ ደግሞ እንደገና ዓይናቸውን ከድነው፥ ደግሞ እንደገና አፍ ላፍ ተያይዘው፥ ደግሞ እንደገና አንድ ላይ ተዋህደው፥ ደግሞ እንደገና ወዳገኙት አዲስ ዓለም ሄዱ።“

-ፍቅር እስከ መቃብር | ከሐዲስ ዓለማየሁ | ገጽ 317-318

******

******

“….አባቴ፥ “እኔ አባትህ ከትልልቅና ካዋቂ ሰዎች ጋር የምውል ነኝ። አንተም እንደ እኔ መሆን ይገባሃል። ዝናና ክብር ቀላል ነገር አይምሰልህ። ከሜዳ ላይ አይታፈስም። … የምታመጣት ልጅ ከጨዋ ቤተሰብ የተወለደች፣ ዘርና ትውልዷ የታወቀና የጠራ መሆን አለበት። ወይራ ከወይራ ነው፤ ስንዴ ከጓያ አይቀየጥም። “ከመልኮስኮስ መመንኮስ” ሲባል አልሰማህም እንዴ? “የማንንም ስድ-አደግና ቅሬ ከየትም ለቅመህ ዝናና ክብሬን ብታጠፋት አደባባይ አውጥተህ የገደልከኝ ያህል እቆጥረዋለሁ። … ምኞትህ ሁሉ ልክስክስ አይሁን።” ብሎ ቁጭቱን ለመግለጽ ያህል ራሱን ነቀነቀ። …

“ማንንና እንዴት ለማግባት እንደምፈልግ ለመግለጽ እስከምችል ድረስ የመዘጋጃ ጊዜ ቢሰጠኝና ከራሴ ጋር ብመክር ጥሩ ነው። እኔ ግን ከአንዳንድ ሁኔታዎች በስተቀር “ማነኛውም ሰው በተፈጥሮ ዓይን ሲታይና ሲመዘን እኩል ነው” በሚለው አምናለሁ።” ብዬ እምነቴን ገለጽኩ።“

-የወድያነሽ | ከኃይለመለኮት መዋዕል | ገጽ 89

******

******

“ውሎ አድሮ፥ በማግስቱም፥ በሳልስቱ፥ በሳምንቱም፥ ሳያዩት ስለ ሰነበቱ ቢያስጠይቁ፥ ቤቱ ሳይከፈት፥ ተዘግቶ መሰንበቱን ሰሙ። ወዲያው፥ በተመሳሳይ መክፈቻ አስከፍተው ቢያዩ፥ በሻህ የለም! አንድ የተዘጋ ኤንቬሎፕ ብቻ፥ በጠረጴዛው ላይ ማስመሪያ ተጭኖበት ይታያል። በላዩ፥ “ለክቡር አቶ ማንደፍሮ ባንቴ” ተብሎ ተጽፎበታል። አቶ ማንደፍሮ፥ ቀ—ስ ብለው እንደ ታቦት በጥንቃቄ አነሱና እሽጉን ከፍተው አነበቡት።”
-የልም እዣት | ከሐዲስ ዓለማየሁ | ገጽ 219

******

******

ዘነበ ወላ፦ “ጋሼ፣ የማርክስን ፍልስፍና አንብበው የሰው ልጆች አልተረዱትም ወይስ ተግባራዊነቱ ላይ ነው ያልሰመረላቸው?”

ስብሐት፦ “ይኸውልህ፣ እንደ ማነኛውም ወንጌል ነው የማርክስ ወንጌል። ለድሆች ደህንነት የቆመ ነው። ከኢየሱስ ወንጌል የሚለየው በአንድ ነገር ብቻ ነው። ይኸውም ገነትን እዚሁ መሬት ላይ እንዘረጋለን ይልሃል ማርክስ። ሠራተኛው መደብ ያሸንፋል ነው ትንቢቱ። አብዮታዊ ፓርቲ ለጭቁኑ አገልግሎት ነው የሚዋቀረው።”

ዘነበ ወላ፦ “ለተከተሉት ሰዎች የማርክስ ፍልስፍና በተግባር ሊተረጎም ይችላል ነው የምትለኝ?”

ስብሐት፦ “ሊተረጎም ካልቻለ የማይቻል ቢሆን እኮ ነው። እንጂ ማርክስ ሃሳቡ በጣም ልክ ነበር። ሃሳቡን እንይ። ከሁሉም እንደችሎታው ለሁሉም እንደሚያስፈልገው ነው የሚለን። ኅብረተሰብ እንደ አንድ ሰው ሆነ ማለት ነው። ሀብቱ በሙሉ የጋራ ነው። ለማንም አናዳላም። ድል ስናደርግ መደብ አይኖርም ወገን አይኖርም። እንደዛ ነው ትንቢቱ። ለእኔ ህልም ነው። ግን ሰው ያለ ህልም አይኖርም።

‘እኔ ቀርቶ እኛ ሆኗል’ በማለት ማርክሲስት ነን የሚሉ ፓርቲዎች አዲስ ገዢ መደብ ሆኑ። ምንም አልተለወጠም። እነሱም የሚፈልጉትን ያገኛሉ ህዝቡም ለጥቂቱ ነገር ይሰለፋል። ‘ይበልጥ ሲለወጥ ይበልጥ ያው ነው’ ይለናል ፈረንሳይ።

የአሜሪካ ሠራተኞች ግን ማርክሲዝምን በሥራ ላይ አዋሉት። ተደራጁ። ሕገ መንግሥታዊ መብታቸው እንዲከበር በሥራ ማቆም አድማ ጠየቁ። የሥራ ሰዓታቸው በቀን 8 ሰዓት ብቻ እንዲሆን ታገሉና አሸነፉ። ዝቅተኛው የቀን ሠራተኛ ደመወዙ በቀን ቢያንስ 10 ዶላር እንዲሆን ሠራተኛው በጥፋት ካልሆነ ከሥራው ቢሰናበት ካሣ እንዲያገኝ የተደረገው በአሜሪካን ሀገር ነው። በእስፖንዳ ማርክሲዝምን በደንብ ተጠቀሙበት።”

ዘነበ ወላ፦ “የፓርቲ አባል ነበርክ?”

ስብሐት፦ “የፓርቲ አባል አልነበርኩም! ብሆን ጥሩ ነበር። እኔ ግን ‘atheist’ አይደለሁም … በእግዚአብሔር አምናለሁ … ፓርቲው ደግሞ እግዚአብሔር የለም ይላል … ስለዚህ እኔ ለመንግሥት በመሥራት ማገልገል እንጂ በሃይማኖቴ ምክንያት የፓርቲው አባል ልሆን የተፈቀደልኝ አይደለሁም አልኳቸው። ተውኝ።”

ዘነበ ወላ፦ “የማሌ ጥናት ተብሎ በየመሥሪያ ቤቱ የውይይት ክበብ ስብሰባ ይካሄድ ነበር። በውቅቱ እንድትሳተፍ ተጠይቀህ አታውቅም?”

ስብሐት፦ “ምንድነው ማሌ?”

ዘነበ ወላ፦ “የማርክሲስት ሌኒንስት ፍልስፍና ውይይት”

ስብሐት፦ “በፍጹም። እነሱም አያስገድዱኝም። እኔም አልቀላቀላቸውም።

ሰውየው ካርል ማርክስ አሪፍ ፈላስፋ ነበር። ሰዎቹ ግን ሳይገባቸው ፈተፈቱት። ፍትፈታውንም ውይይት ክበብ አሉት።”

ዘነበ ወላ፦ “የቤተ ክህነት ሰዎች መጥተው አቶ ስብሐት ይምጡ እስቲ ዘር ማንዘሮት የቤተክርስቲያኒቱ አገልጋይ ነበሩ። እርሶም የዘር ማንዘሮን ክርስትያናዊ ግዴታ ለመወጣት ቤተክህነቷ ትፈልጎታለች። መጥተው ያገልግሏት ቢሉህስ?”

ስብሐት፦ “የእኔን ተፈጥሮ ልብ በል። አንድ ‘formula’ ተከትሎ ያችኑ መደጋገም ደስ አይለኝም። በክርስትና በእስልምና በፖለቲካ ፓርቲም እያልክ ብታጠናቸው አማኞቻቸውን ደንግገው የሚይዙበት ሕግጋት አላቸው። ያ ደግሞ ሼል ሆኖ እንደ ዕንቁላል ቅርፊት ሌላን የምታይበትን ዓይን ይጋርድሃል። ስለዚህ ምንም ዓይነት የፖለቲካም ሆነ የሃይማኖት ድርጅት ተከታይ መሆን አልፈልግም።

አባቶችን፣ ቤተክህነትን ማገልገል ከአማኝ የሚጠበቅ ነው … እናንተም ከልባችሁ ቤተክህነቷን እያገለገላችኋት ነው … እኔም እንደናንተ እንዳላገለግል ‘atheist’ ነኝ እላቸዋለሁ።”

-ማስታወሻ (ስብሐት ገብረእግዚአብሔር) | ከዘነበ ወላ | 1993 ዓ.ም ታተመ | ገጽ 203-205

******

******

ወዳጅነት
የጣልኩትን ፍለጋ
ያየሁትን እንዳልዘነጋ
ምስጢር በብዕር ጫፍ ልወጋ
ሁል ግዜ ‘ፅፋለሁ።
“ሞኝና ወረቀት…” እንደሁ
………..ወረት የላቸው!
— ለምን? | በአገኘሁ አዳነ ድልነሳሁ | ገጽ 35 | ታተመ 1999

******

******

[…] ሌት ከዋክብቱ እንደፀደይ
አጥለቅልቆን በቀይ አደይ
ሰማዩ ሥጋጃ አጥልቆ
ተሽለምልሞ አንጸባርቆ
ፈክቶ፥ አሸብርቆ ደምቆ
በአዝመራ፥ በአጥቢያ ዐፀድ ሰፍኖ
የዓደይ አዝርዕት ተከሽኖ
በዕንቁጣጣሽ ሰብል ታጥኖ
ኢዮሃ አበባዬ ሆኖ፥
ጨረቃዋ ከቆባዋ፥ ከሽልምልሚት እምቡጧ
ጧ ብላ ከሰንኮፈንዋ፥ ተንዠርግጎ የእንኮይ ቡጧ፥
ድንግል ጽጌ-ረዳ ፈልቃ
ፍልቅልቂት ድምቡል ቦቃ …
ተንሠራፍታ የአበባ ጮርቃ፥
ታድያን ብሌኑ የጠጠረ
ባሕረ-ሃሳቡ የከረረ
የውበት ዓይኑ የታወረ
ልበ-ሕሊናው የሰለለ
አይ፥ አበባ አይደለም አለ፤
አይ፥ እሳት አይደለም አለ፤
ያልታደለ። …
ሰማይ ጨለማ ነው እንጂ፥ እሳት አደል ብሎ ካደ
እቶን ባይኑ እየነደደ።
ከዋክብቱ እንደ ችቦ
በነበልባል ወርቀ ዘቦ
ከፅንፍ ፅንፍ አውለብልቦ
ደመራው እየተመመ
እየፋመ እየጋመ
ደመና እንደንዳድ ሲነድ
መንጸባርቅ ሰደድ ሲወርድ፥
በራሪ ኮከብ ተኩሶ
በአድማሳት እሳት ለኩሶ…
ይኸ እንደኔና እንዳንቺው፥ የውበት ዓይኑ የሰለለ
ሰማይ ጨለማ ነው እንጂ፥ እሳት እኮ አይደለም አለ፥
ያልታደለ። …… ይቅር ብቻ አንናገርም፥
እኔና አንቺ አንወያይም፤
ለውይይት አልታደልንም
እንዲያው ዝም፥ እንዲያው ዝም … ዝም።
አበባ አንሆን ወይ እሳት
ተጠምደን በምኞት ቅጣት
ሰመመን ባጫረው መዓት
ዕድሜአችንን እንዳማጥናት፤ …እሳት አንሆን ወይ አበባ
በሕቅ እንቅ ስንባባ
ባከነች ልጅነታችን፥ እየቃተትን ስናነባ
ሳንፈጠር በሞትንባት
ሳናብብ በረገፍንባት
ሳንጠና ባረጀንባት
አበባ ወይንም እሳት፥ መሆኑን ብቻ አጣንባት።

-እሳት ወይ አበባ | ከጸጋዬ ገብረ መድኅን | 1960/1999 ዓ.ም ታተመ | ገጽ 152-154

******

******

ዘነበ ወላ፦ “በአንተ የወጣትነት ጊዜ በአማርኛ ሃሳብን መግለፅ አይቻልም ብላችሁ አንተም ሆንክ ጓደኞችህ በእንግሊዝኛ መጻፍ የወሰናችሁበት ወቅት እንደነበረ ይነገራል። በኋላ ደግሞ ወደ አማርኛው ተመልሰህ ድንቅ ፀሐፊ ወጣህ። ይህ እንዴት ሊሆን እንደቻለ ብትገልፅልኝ?”

ስብሐት ገብረእግዚአብሔር፦ “በወጣትነቴ አማርኛ በምፈልገው መልኩ ሀሳብን መግለፅ አያስችልም የሚል እምነት ነበረኝ። በዚህም ላይ ያስተማሩን እንግሊዝኛ ተናጋሪዎች መሆናቸውን አትርሣ። እኛ አናውቅም እንጂ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ወጣቱን ትውልድ በቅኝ አገዛዝ ጥበባቸው ይዘውናል። በኋላ ዳኛቸው ወርቁ “አደፍርስን” ጻፈ። እኔ ሣነበው በአማርኛ መፃፍ እንደሚቻል ገባኝ። ስለዚህ በእንግሊዝኛ የመፃፍ ሀሳቤን ተውኩት። በወቅቱ አስታውሳለሁ “ሌቱም አይነጋልኝን” በእንግሊዘኛ መጻፍ ጀምሬው ነበር። 65 የተተየበ ገጽ ላይ አቆምኩት። … አፍሪካውያን ደራሲያን ሀገራቸው የእንግሊዝ ወይም የፈረንሳይ ቅኝ ግዛት ስለነበረ በገዢው ቋንቋ ነው እያነበቡ ያደጉትና የሚፅፉት። እኛ ሀገር እንደዚያ ዓይነት ባሕል አልነበረም። አብዛኞቻችን የምንጽፈው በአማርኛ ነው። በእንግሊዝኛ የምንጽፍ ጥቂት ነን።“

-ማስታወሻ (ስብሐት ገብረእግዚአብሔር) | ከዘነበ ወላ | 1993 ዓ.ም ታተመ | ገጽ 238

******

ከአሥመራ ወደ ምፅዋ ለሚወርድ መንገደኛ ምፅዋ ከመድረሱ ሃያ ኪሎ ሜትር ያህል ሲቀረው፥ ተድአሊ የተባለችውን ቀበሌ ያገኛል። ገና ከጊንዳዕ በታች የሚገኘውን ገደላ ገደል ወርዶ የዳማስን ሜዳ እንዳለፈ የሚጋረፈው የቆላ ሐሩር ይቀበለዋል። …

ከሜድትራኒያን አከባቢ የሚነሣው የክረምት ጊዜ በቀይ ባሕር አካባቢ ያሉትን አገሮች ከልሎ በሚወስድበት ወቅት ቃጠሎውና ደረቁ አከባቢ ወደ ለምለምነት ስለሚለወጥ ከጊንዳዕ ጀምሮ እስከ ምፅዋ ያለው ወረዳም ከጥቅምት እስከ ሚያዚያ መጨረሻ ድረስ የሚታይበት ውበት፥ የሚገኝበት የመሬት ፍሬና የአየር ለውጥ የማይጠገብ ነው።

ራስ አሉላም ከጊንዳዕ ወደ ሰሐጢ የወረዱት በጥር አጋማሽ ላይ ነበር። የአየሩ ጠባይ አልፎ አልፎ ዝናብ የሚጥል መሬቱ በልምላሜ የተሸፈነ ነበር። …

ራስ አሉላ፥ በተፈጥሮአቸው ከወረሱት ጸጋ የጦር ስልት ሲያወጡ ወይም ጦርነት ለመግጠም ሲያስቡ የአየር ጠባይንም በቅድሚያ ለማወቅ የሚያደርጉት ጥረት ነው። ሠራዊታቸው በሐሩር፥ በጨለማ፥ በወባ፥ በኃይለኛ ዝናብ ጎርፍና ጉም እንዳይጠመድባቸው እጅግ ይጠነቀቁ ነበር። …

…ራስ አሉላ ከንጋቱ ላይ ሰሐጢ አጠገብ ደርሰው የወታደራቸውን አሰላለፍ በዝርዝር ተመለከቱ። … ፀሐይ ስትወጣ ከጀርባቸው እንድትሆን አደረጉና ጦርነቱን ጀመሩ። … የመድፍና የጠመንጃው ተኩስ ቀረና ውጊያ በጨበጣ ሆነ። ራሳቸው ራስ አሉላ ከፈረሳቸው ወርደው እንደ ተራ ወታደር በተድአሊ ወንዝና ዳገት እየዘለሉ ከጠላት ጦር ጋር ተደባለቁ። … ጉራዕ ላይ በግብፅ ኩፊት ላይ በድርቡሹ አንገት ላይ በደም ያጠቡትን ጎራዴያቸውን መዘዙና የጣልያኑ ጦር መከላከያ ለመሥራት ሲጣደፍበት ወደነበረው ቁብታ ወጥተው ለሸለሹት። …

[…አቀንቃኝ…] ኪዳኔ መብራቱም፥

“ጎራው ተማሙቋል መሬት ተደባልቋል፤
ነጩ ክምር ፈርሶ ምስቅልቅሉ ወጥቷል።
…ሚስትህ ምነው ባየች በሰማች እናትህ፤
በአሉላ ጎራዴ ሲበጠስ አንገትህ።
የነማን አገር ነው ብለው ሳይጠይቁ፤
አገር የደፈሩ እነሆ ወደቁ።
ምነው በጠየቁ የግብፅን ወታደር፤
ምነው በጠየቁት የድርቡሽ ወታደር፤
እንደማይደፈር ያባነጋ መንደር።”

እያለ አቅራራ።“

-አሉላ አባ ነጋ | ከማሞ ውድነህ | 1979 ዓ.ም ታተመ | ገጽ 237-241

******

******

ትዕግሥት ትመስለዋለች። ስታጠና እንደ ነበረችው ረዥም ቀሚሷን ለብሳ፥ በነጠላ ጫማ አጭር ቁመቷ ይብሱን ተጋልጦ፥ በፈገግታ ጉንጮቿን እያሠረጎደች አቤል መኝታ ቤት ድረስ በምሽት ከተፍ!

“ምነው አቤል? ሰው ለምን ታስቸግራለህ? እኔንስ ለምን በፍቅር ታሠቃየኛለህ? ለምን ግልፅ አትሆንልኝም? ማፍቀር’ኮ ነውር አይደለም” ስትለው …

አቤል ግልፅነቷ እየገፋፋውና የተከዘው ገፅታዋ እያሳዘነው፥ “እኔ ምን አደረግኩሽ ታዲያ? ደግሞ ተበዳይ አንቺ ሆንሽ እንዴ? እኔ ምን ያህል እንደ ተቃጠልኩ ውስጤን ገልጠሽ ባየሽው!” አላት።

“አትዋሸኝ አቤል! እውነቱን ንገረኝ። ስታየኝ ግንባርህን የምታኮማትርብኝ፥ ዘግተኸኝ የምታልፈው ለምንድነው? ፍቅር ነው ጥላቻ?”

“የጥላቻ ነገር ለምን ታነሻለሽ? በእኔና በአንቺ መሐል ጥላቻን ምን አመጣው? የማደርገው ሁሉ የፍቅር ነው።”

“ታዲያ እንዲህ በዕውር ፍቅር እንዴት እንዘልቀዋለን፥ አቤል? ሁለታችንም ውጥረት ላይ ያለን ተማሪዎች ነን። እኔን የገና ማዕበል እየጠበቀኝ ነው። አንተም መመረቂያ ዓመትህ ነው። ግልፅ ካልሆንን እኮ ሁኔታችን ለሁለታችንም ግብ መሰናክል ነው።” …

… ከእንቅልፉ ባነነ። እንቅልፍ ዓይን መጨፈን ብቻ በሆነና፥ ከትዕግሥት ጋር ካገናኘው ሕልሙ ላለመንቃት ዕድሜ ልኩን አይኑን በጨፈነ ምን ነበረበት! …“

-ሰመመን | ከሲሳይ ንጉሡ | 1978 ዓ.ም ታተመ | ገጽ 113-117

******

******

ማሞ ቂሎ

“ተማር ልጄ” ሲሉት አይሰማም አይሰማም
“ሥራ ልጄ” ሲሉት አይሰማም አይሰማም
ያርባ አመቱ ህጻን ካልመቱት አይሰማም
ካልመቱት አይሰማም ካልቆነጠጡት
ወይ ካላስፈራሩት በቃላት አለንጋ በቃላት ብትር
ሥራውን አይሰራ ትምህርት አይማር።

እድሜው ረጅም ነው ሰላሳ አርባ ሃምሳ
ልምድ ያላስተማረው ያምሮ ኮሳሳ
ሥራውን አይሰራ
ወሬ እየፈተለ
ወሬ እያደራ።

ታይፑ አይመታ
ጭቃው አይቦካ
መንገዱ አይሰራ
በልግም ለገማ።

ፊርማው አይፈረም
ሒሳብ አይቆረጥ
ቤቱ አይጠረግ
በኪስ ኪስ ተብሎ
ኪሱ ሳይታሸግ።

ህጻን ያርባ አመቱ ሥራውን አይሰራ
ካላስደነገጡት በቃላት አለንጋ
በብትር ባርጩሜ ባርጩሜ ባለንጋ።

አያ ጎሽሜ | ከፈቃደ አዘዘ | 1973

******

2 Responses to “Ethio Books World”

 1. Yene yan said

  Satsfaction

 2. abebe said

  betam arifnew lemambeb yaberetatal

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: