Ethio Tribune

Plural News and Analysis on Ethiopia and HOA

 • RSS google news

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS Capital

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS Unknown Feed

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS Unknown Feed

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS Walta

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS DireTube Video

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • Enter your email address to receive notifications of new posts

  Join 481 other followers

 • Meta

 • Articles

 • ምስለ መለስ፡ የማንነቱ ገፅታ

  ምስለ መለስ፡ የማንነቱ ገፅታ

 • Live streaming

 • ETV live streaming
 • RSS Sudan Tribune

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS East Africa News

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS BBC News

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS Aljazeera

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS Climate Change News

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS Technology News

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • Archives

 • Flickr Photos: Ethiopia

የፕ/ር መስፍን የ‹አባይ ጦርነት› ግልብ ትንተናና ምክር

Posted by Ethio Tribune on June 9, 2013

By Daniel Berhane

ፕ/ር መስፍን ወልደማሪያም ባለፈው ሳምንት ከአባይ ጉዳይ በተያያዘ የጦርነት ቅስቀሳን ለመገሰጽና የግብጽን የጦር ሀያልነት ‹ለማሳወቅ› አንድ ጽሑፍ አስነብበውናል፡፡

ጽሑፉ በጥድፊያ እና/ወይም እንደተለመደው የኢሕአዴግን ባለስልጣኖች ለማብሸቅ ተብሎ የቀረበ ስለመሰለኝ አላተኮርኩበትም ነበር፡፡mesfin woldemariam

ነገር ግን እሳቸው የጽሑፋቸውን ግልብነት (shallowness) አስተውለው – ጠለቅ ያለ ማብራሪያ በመስጠት ለማጠናከር ወይም ለማስተባበል ይሞክራሉ ብዬ ስጠብቅ፣ ትችት የሰነዘሩባቸውን ሰዎች በመሀይምነት መፈረጅ ነው የመረጡት፡፡

ሰለሆነም እንደው ምናልባት እሳቸውም ሆነ መስፍን ህፀጽ አይገኝባቸውም ብለው የሚያምኑ የሚመስሉት ደጋፊዎቻቸው ልብ አላሉት እንደሆን ለማስገንዘብ፤ ስለፕ/ር መስፍን ጽሑፍ አንድ ሁለት ልበል፡፡

የ ጽሁፉ ዋነኛ ጭብጥ በሚከተለው ጥቅስ ይወከላል፡፡

‹‹ጦርነት እንኳን ገና በልቶ ላልጠገበ ሕዝብና ለጥጋበኞቹም አይመጭም፤ የተራበ ሕዝብ በጠገቡ መሪዎች ሲነዳ ግን ጦርነት ለአጉል ጀብደኛነት ዝና የሚጠቅም መስሎ ይታያቸዋል፤……ለፍቅር መተዋወቅ እንደሚያስፈልግ ሁሉ ለጠብም መተዋወቅ ያስፈልጋል፤ የተሟላ መረጃ ቢኖረን የጥንት ታሪክ እየጠቀስን ሰዎችን ለጦርነት እንቀሰቅስም ነበር ብዬ አምናለሁ፡፡ ››

የትኛው ‹የጠገበ› ባለስልጣን ነው ለጦርነት የቀሰቀስው?

የመንግስት ባለስልጣኖች አንድ ሁለት ጊዜ – ከ2 ዓመታት በፊት – ‹‹ግብጽ ብትወረንስ›› የሚል ጥያቄ ሲቀርብላቸው ታሪክ ጠቅሰው እንደማይፈሩ መግለፃቸውን አስታውሳለሁ፡፡ (ግን ሌላ ምን መልስ ሊሰጡስ ይቻላቸዋል?) ከዚያ ባለፈ ግን ግብጽን አስመልክቶ አዎንታዊ እንጂ አሉታዊ ዘገባ እና ቅስቀሳ በመንግስት ሚዲያ ሰምቼ አላውቅም፡፡

እንዲያውም ከካይሮ ግድም አሉታዊ ወሬ በመጣ ቁጥር የመንግስት ባለስልጣኖች ጦርነትና ግጭት የመከሰት ዕድሉን ስለሚያጣጥሉ፣ አንዳንድ ታዛቢዎች ‹‹እነዚህ ሰዎች አስጠንቁለዋል እንዴ›› ያሉበት ጊዜ አለ፡፡ ለምሳሌ – ከአንድ ወር በፊት የጠ/ሚኒስተሩን ቃል-አቀባይ ጌታቸው ረዳን ሳናግረው ‹‹ግድቡን እንደማናቆም ሲያውቁ ራሳቸውን ከእውነታው ያስታርቃሉ›› ነበር ያለኝ፡፡

እርግጥ መንግስት በይፋ የሚያሳየው መተማመን ስልታዊ ሊሆን ይችላል፡፡ ግብጾችንም ‹‹ማነው ከግድቡ ጀርባ ያለው?›› የሚያሰኛቸውም እሱ ሳይሆን አይቀርም፡፡

ሌላው የጽሑፉ አንኳር ሀሳብ እንዲህ ይነበባል፡-

‹‹አንዳንድ አስፈላጊ መረጃዎችን ላቅርብ፤ — የግብጽ የጦር ኃይል በዓለም አሥረኛ ነው፣ በአፍሪካና በመሀከለኛው ምሥራቅ የሚወዳደረው የለም፤ አንድ ሚልዮን ተኩል ያህል የጦር ኃይል አለው፤ በዓየር ኃይልም ከዓለም አሥራ አራተኛ ነው፤ በታንክ ብዛት አራተኛ ነው፤ በባሕር ኃይል ሰባተኛ ነው፤ በጦር በጀት አርባ ሦስተኛ ነው፤››

የመረጃ ምንጩን ባይጠቅሱም ከመጠነኛ አሰሳ በኋላ እንደተገነዘብኩት መረጃውን ያገኙት ከGlobalFirePower.com ነው፡፡ የዌብሳይቱን የደረጃ አሰጣጥ ስልት ከተረዳሁ በኋላ ግን መስፍን ጽሑፋቸውን በችኮላ እንደጻፉት ደመደምኩ፡፡

ከGlobalFirePower.com ደረጃዎች ጥቂቶቹን በምሳሌነት ላቅርብ፡-

* የእያንዳንዱን ሀገር ጠቅላላ የጦር አይሮፕላን (ጀት፣ ሔሊኮፕተር፣ ወዘተ) ብዛት በመቁጠር፡- በአየር ሀይል ለኢራን 5ኛ፣ ለሳውዲ አረቢያ 11ኛ፣ ለግብጽ 14ኛ፤ ለእስራኤል 20ኛ ደረጃ ይሰጣል፡፡

* በባሕር ኃይል (ሁሉንም የባህር ላይ የጦር ተሸከርካሪዎች በመቁጠር) በሰጠው ደረጃ ግብጽ ሰባተኛ ደረጃ በመያዝ ከቱርክ ከፈረንሳይ ከጣልያን ከሕንድና ከእንግሊዝ ትበልጣለች፡፡

* በታንክ ብዛትም የግብጽ ደረጃ ከህንድ ከሩሲያና ከፈረንሳይ በላይ ነው፡፡

* የግብጽ ወታደር ብዛትም (ግማሽ ሚሊዮን ቋሚና 1 ሚሊዮን ተጠባባቂ ወታደር በመያዝ) ከፈረንሳይ ከእንግሊዝና ከእስራኤል ይበልጣል፡፡

ይህን የደረጃ  አሰጣጥ መሠረት አድርጎ የወታደራዊ ሀያልነትን መመዘን አሳሳች መሆኑ ለማንም ግልጽ ስለሆነ ብዙ አልልም፡፡

ያም ሆነ ይህ ግን የኢትዮጲያ ጦር ሀይል የወታደር ቁጥር እና የበጀት መጠን ውስን እንዲሆን የተደረገበት ሳይንሳዊ መነሻ ሲኖረው፤ ግብጽ ደግሞ የጦር ሀይል ብዛትና ወጪ ማብዛት የፈለገችበት የፖለቲካ ምክንያት ለግማሽ ክፍለ-ዘመን ከቆየው ከፊል-ወታደራዊ ስርአቷ ባህርይ ጋር ይያያዛል፡፡

ይልቁንስ ፕሮፌሰሩ ሊያነሱ ይገባ የነበረው ጥያቄዎች፡-

* በዚህ ዘመን የጦርነት መነሳት ሆነ ውጤት በጥይት ብዛት ነው እንዴ የሚመሠረተው? (የዲፕሎማሲ፣ የኢኮኖሚ፣ የinternational public opinion ወዘተ ወሳኝ ሚናስ)

* እኛ እና ግብጽ እኮ የጋራ ድንበር ስለሌለን፤ ግብጽ ሺህ ኪሎሜትሮች ተጉዞ ለሚደረግ ጦርነት በቂ ክህሎት፣ ልምድ፣ ድርጅት እና ሎጂስቲክ አላት ወይ?

* ሱዳን ወይም ኤርትራ በሺዎች የሚቆጠር የግብጽን ሠራዊት ለማስፈርና ለማሳለፍ ይፈቅዳሉ ወይ?

አንዳንድ ሰዎች፣- ውስን የዓየር ወይም የኮማንዶ ጥቃት(surgical attack) ሀሳብ በማንሳት የመስፍንን ጽሑፍ ለማሻሻል ይሞክራሉ፡፡ እዚህ ላይም የቴክኖሎጂ ጥያቄ አለ፡፡ ከካይሮ ተነስቶ ኢትዮጲያ ደርሶ የሚመለስ አይሮፕላን ግብጽ አላት? (ስለሌላትም) የሱዳንን ዓየር ክልል ጥሶ መብረር ብቻ ሳይሆን ማረፊያም ማግኘት ትሻለች፡፡ እናስ ሱዳን ትፈቅዳለች?

አንድ ነገር ልብ በሉ፡- ግድቡ ሲያልቅ ለማፍረስ ጥቂት ከባድ ቦንቦች ወይም ፈንጂዎች ሊበቁ ይችላሉ፡፡ ዛሬ ላይ ግን ማጥቃት የሚያስፈልገው እንዳለ የፕሮጀክት ሳይቱን ይሆናል፡፡ (ገና በጅምር ላይ ያለን ቤት ማጥቃት እና ተሠርቶ ያለቀን ቤት ማጥቃት አድርጋችሁ እዩት)

እነዚህንና ሌሎች ተዛማጅ ጥያቄዎች ሳይመልሱ ታንክ መቁጠር ግልብ ትንተና ይሆናል፡፡

ለማንኛውም ከሀይማኖታዊ ወይም ፈሪሀ-እግዚያብሔር በመነሳት በድፍኑ ‹ጥጋብ ውርደት ያስከትላል› ብሎ መናገር ቢቻልም፤ የፕ/ር መስፍን ጽሑፍ ግን የመንግስት ሀላፊዎች ‹ጠግበው› ለጦርነት መቀስቀሳቸውን ሆነ ‹ጥጋባቸው› ‹ውርደት› እንደሚያስከትል በበቂ አላስረዳም፡፡

እርግጥ የግብጹ Al-Jamaa al Islamiya መሪ ኢትዮጲያ በአባይ ላይ የምትሠራው ሥራ የጦርነት አዋጅ ነው በማለት አፀፋውን ለመመለስ ዛቻ ብጤ አሰምቷል፡፡

ፕ/ር መስፍንም የ‹ጠገቡ መሪዎች ለአጉል ጀብደኛነት ዝና› እየነዱን እንዳሉ አድርገው የቆጠሩት የሕዳሴ ግድብ ሥራን ይሆን እንዴ?

13 Responses to “የፕ/ር መስፍን የ‹አባይ ጦርነት› ግልብ ትንተናና ምክር”

 1. drte said

  mekshef ende mesfin w/mariam!!

 2. Wonder said

  Who is professor Mesfen- I think this old man ,trading with name of intellectuals ,he was always sicking with his old analysis and a Fable tale history.

 3. Anonymous said

  In both total military hardware and standing army, the Arab World far outweigh the Israeli’s standing! Has the prof. forgotten the outcome of the Israeli-Arab War in 1967? The Arabs were soundly beaten by the tiny Israeli military! Although Ethiopian does not claim to be like the Israelis, when it comes to threat of the Motherland, Ethiopians stand second to none in the world!!!

 4. menbe pilatos ramp said

  a tink the so called pr.mesfin does not have a plan annd know nothing about the purpose of being living in this world!he is just idle

 5. goldenboyh said

  ኣንድ ነገር ልብ ልንለው የሚገባንን ቢኖር ከስብእናችን / ለፕ/ር ፕሮፌሶርን የሚያሸተውን እና ትክክለኛው ከኛ የሚጠበቅ ወይም የሚዛመድ/ ወሬ ብናወራስ ምናለበት፡፡ ፕሮፌሶርን ሚያከለ መኣረግ ይዘህ ከ KG ተማሪ የማይጠበቅ ወሬ ማውራት ራሱ ውርደት ነው፡፡በዛላይም ስለ ውልቀ ጥቅም ሳይሆን ሰለ ኣገር ጉዳይ ነው! የሚወራ ያለው፡፡ ያን ከ ኣፍምጫ ኣርቆ የማያሳይ እውቀት ተይዞ ከ80 ሚሊዮን ለባይ ህዝብ እንመራለን ማለቱ በራሱ ኣጉል ኣሰተሳሰብ ነው፡፡

 6. Anonymous said

  ፕሮፌሰር የሚል ማኣርግ ኣህያን በመጠበቅ ነው እንዴ የተሰጣቸው? የኣህያ ኣስተሳሰብ ነው ያላቸው

 7. Anonymous said

  ፕ/ራችን ኣብደዋል ልበል እንዴ

 8. Berhanu said

  He tried 2 explain nothing 4 nothing

 9. miki said

  ነገሮችን አገናዝቦ የሚተነትን ሰው እንደሌለን ያወቅነው «ፕሮፌሰር» በሚል ስም ለዘመናት ተደብቀው ጥሩ መካሪ በመምሰል ሕዝበ እውቀት ጠምን ሲያሳስቱ ነው። እርሳቸውን በመከተል አዋቂ ለመምሰል የሚፈልጉ ብዙዎች ከመምህሩ ደቀመዝሙሩ ሆነው ሀገር ሲያምሱ ቆይተዋል። ዛሬም እያመሱ ነው። እና እባካችሁ ለአንዲት ደቂቃ እውቀትን ከማመዛዘን ጋር እንዲሰጣችሁ ተግታችሁ መረጃዎችን ፈትሹ ማለት ይሻላል።

 10. zam said

  ፕሮፌሰሩ ጨርሰው ያበዱ ይመስላሉ፡፡ ካለ እርሳቸው በዚህ ሀገር አዋቂ የለም፡፡ ያሳለፉትን ዘምን አበላሽተው መጪውን ዘመን ለማበላሸት ሲሞክሩ ለዚህ ትውልድ ያላቸው ንቀትን ያመላክታል፡፡
  “ምሁር ነኝ” ባዩ ፕሮፌሰር ባሳለፌት በርካታ አስርት ዓመታት የሁሉንም መንግስታት እኩያ ሆነው ሲሳደቡና እኔ ብቻ አዋቂ ሲሉ ለትውልዳቸው ሆነ ለቀጣዩ ትውልድ ምንም ምሁራዊ ስራ ሳይሰሩ ጊዚያቸው በከንቱ ያከሸደፉ ይመስላሉ፡፡
  ሰው እድሜ እየጨመረ ሲሄድ እየሰከነና ለትውልድ እያሰበ ይሄዳል እንደደንቡ፣ የፕሮፍሰር ነገር ግን የተገላቢጦሽ ነው ፡፡ እንደመካሪ አስታራቂ ተንኳሽና እና ሸረኛ፤ እንደ ይቅርባይና ቻይ ቂመኛ እና ነውጠኛ መሆን ምን ይሉታል፡፡
  የሚያወሩት አያውቁምና……

 11. Anonymous said

  I think he is not an Ethiopian. He doesn’t love his country. he is fake and illetrate person. because as far as I know learning is permanent change in behaviour. that is why I said he is illetrate

 12. Anonymous said

  Shame on professor Donkey

  • Anonymous said

   insults are not good here ,the good thing is either to accept his idia or to reject it logistically ,,,,, insults …..bad any way

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s