Ethio Tribune

Plural News and Analysis on Ethiopia and HOA

 • RSS google news

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS Capital

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS Unknown Feed

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS Unknown Feed

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS Walta

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS DireTube Video

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • Enter your email address to receive notifications of new posts

  Join 481 other followers

 • Meta

 • Articles

 • ምስለ መለስ፡ የማንነቱ ገፅታ

  ምስለ መለስ፡ የማንነቱ ገፅታ

 • Live streaming

 • ETV live streaming
 • RSS Sudan Tribune

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS East Africa News

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS BBC News

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS Aljazeera

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS Climate Change News

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS Technology News

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • Archives

 • Flickr Photos: Ethiopia

“ህወሓት የታጋለው የህወሓትን ስርወ መንግስት ለመፍጠር ሳይሆን ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመፍጠር ነው” አቶ በረከት ስምኦን

Posted by Ethio Tribune on September 19, 2012

አርብ እና ቅዳሜ (መስከረም 5 እና 6 ቀን 2005 ዓ.ም) ባካሄደው ጉባኤ በሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ምትክ የግንባሩን አመራሮች መርጧል። በአመራር ምርጫውም የደኢህዴን ሊቀመንበር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የግንባሩ ሊቀመንበር ሆነው ሲመረጡ፤ የብአዴን ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ደመቀ መኮንን ደግሞ የግንባሩ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል። የአመራር ምርጫውን አካሄድና ምርጫውን ተከትሎ ስላሉት የተለያዩ አስተያየቶች እንዲሁም በጥቂት ሀገራዊ ርዕሰ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሚኒስትርና የኢህአዴግ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የሆኑትን አቶ በረከት ስምኦንን ባልደረባችን ዘሪሁን ሙሉጌታ በቴሌፎን አነጋግሯቸዋል።

ሰንደቅ– ከሰሞኑ የተካሄደው የኢህአዴግ ም/ቤት ስብሰባ አቶ መለስ ዜናዊ ከዚህ ዓለም በሞት ከመለየታቸው በፊት ትተውት ባለፉት ሰነድ የአመራር መተካካቱ መፈፀሙ ተነግሯል። ይሄ ሰነድ ምንድነው?
አቶ በረከት፡- አቶ መለስ በህይወት በነበሩበት ወቅት በድርጅታችን ታሪክ ውስጥ ብዙ ሰነድ ነው ያዘጋጁት። ብዙ የትንተና ማቴሪያሎች አዘጋጅተዋል። አሁን ደግሞ በመጨረሻ የድርጅት ግንባታ አመራራችንን የሚመለከት ከዚህ በፊት በተለያዩ ሰነዶች ውስጥ ያቀረቧቸውን አሰባስበው ይበልጥ አዳብረው ያቀረቡት ሰነድ አለ። በእርግጥ ይሄንን ሰነድ ያዘጋጁት ለአሁኑ ምርጫ አስበው አይደለም። ኢህአዴግ በጠቅላላ በሀገር ደረጃ ብቃት ያለው ኢትዮጵያን የሚለውጥ አመራር እየገነባ እንዲሄድና እስካሁን የመጣበትን የትግል መድረክ አጠናክሮ ወደፊትም በዚህ ደረጃ የሚጠብቀውን ፈተናዎች ሁሉ በድል አድራጊነት እየተወጣ እንዲሄድና ድርጅቱም የአመራር አቅም እየኮተኮተ እንዴት ይቀጥላል የሚለውን ጥያቄ የሚመልስ ሰነድ ነው። ስለዚህ አቶ መለስ ያዘጋጁት ሰነድ ለዚህ ለአዲሱ አመራር ምርጫ ተብሎ ሳይሆን በአጋጣሚ አቶ መለስ በህይወት በነበሩበት ጊዜ የድርጅቱ ሥራ አስፈፃሚ አካላት የተወያዩበት ሰነድ ነበር፤ እሳቸው በህይወት እያሉ በሚቀጥለው ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ቀርቦ እንመካከርበታለን ተብሎ ቀጠሮ የተያዘበት ሰነድ ነበር።
ሰንደቅ፡- ስለዚህ ለአመራር ምርጫው ይሄንን ሰነድ በግብአትነት ተጠቅማችኋል ማለት ነው?
አቶ በረከት፡- አይደለም። ሰነዱ ከአሁኑ አመራር ምርጫ ጋር የሚያያዝ ነገር የለውም። ሰነዱ በጠቅላላ በድርጅቱ የአመራር ግንባታ የሚመራበት ሰነድ ነው።
ሰንደቅ፡- የአመራር ምርጫው በምን መልኩ ተከናወነ? የኀሳብ ልዩነት፣ ፍጭት ወይም የጋራ መስማማት ነበር፤ እንዴት ተከናወነ?
አቶ በረከት፡- የኅሳብ ልዩነት አልተከሰተም። የሁሉም ስምምነት የነበረባቸው ጉዳዮች አሉ። በመጀመሪያ ይሄ ጉዳይ ትንሽ ነገር ነው። ኢህአዴግ ትልቁ ኃላፊነቱ ወንበር መከፋፈል አይደለም። የኢህአዴግ ትልቁ ኃላፊነት ሀገር መለወጥ ነው። ስልጣንም ቢሆን በስልጣንነቱ ሳይሆን የሚታየው ሀገር በመለወጥ መሳሪያነቱ ነው የሚታየው የሚል የጋራ መግባባት እንጂ ብዥታ አልነበረም። ስለዚህ ወንበርን ለወንበርነቱ አይደለም የምንፈልገው። ሀገር የሚለወጠው ደግሞ በአንድ ሰው አይደለም። የጋራ ስራ ነው።
ሰንደቅ፡- በአሁኑ ወቅት ከፊት ያለውን አመራር በማየት ቀደም ሲል የነበረው የህወሓት የበላይነት ቀንሷል የሚል ፍራቻ እየታየ ነው፤ ስለዚህ ጉዳይ ምን ይላሉ?
አቶ በረከት፡- በመጀመሪያ ደረጃ በግልፅ የሚታይ ፍራቻ (Frustration) አላየንም። የሚታይም አይመስለኝም። የማይታይበት ምክንያት ህወሓት በአፄ ምኒልክና እና በደርግ እንዲሁም በአፄ ኃይለስላሴ የነበረውን ሥርዓት አምርሮ ሲታገል የቆየው የህወሓት ስርወ መንግሰትን ለመፍጠር አይደለም። ህወሓት የታገለው ዴሞክራሲያዊት የሆነች ኢትዮጵያን ለመፍጠር ነው። ያንን ሁሉ መስዋዕትነት የከፈለውም ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመፍጠር ነው። ስለዚህ ህወሓት የታገለው ምርጫ በዴሞክራሲ አኳን የሚካሄድበት፣ ሀገሪቱ መሪዎቿን በነፃ የመትመርጥበት ሥርዓት እንዲገነባ ነው። ስለሆነም የሰሞኑ የኢህአዴግ ምርጫ የህወሓት የትግል ውጤት ነው። የትግራይ ሕዝብ የትግል ውጤት ነው። የተከፈለው መስዋዕትነት መና እንዳልቀረ የሚያሳይ ነው። እውነት ለመናገር ህወሓቶች በከፍተኛ ደረጃ የኮሩበት ቀን ቢኖር አሁን ነው።
ሰንደቅ፡– ሰሞኑን የተሰጠው የጀነራሎች ሹመት አሁን ካለው አዲስ አመራር ምርጫ ጋር የሚያገናኘው ነገር አለ?
አቶ በረከት፡- ለእኛ ለኢህአዴጎች ይሄ የስልጣን ክፍፍል ምርጫና የመሳሰሉት ነገሮች እጅግ በጣም ትንሹ አጀንዳችን ሆኖ ነው የከረመው። ይሄ ጉዳይ ትልቅ አጀንዳቸው የሆነና እያንዳንዷን ድርጊት ከምርጫው ጋር እያያያዙ ሲያስሩና ሲቀጥሉ የሚውሉ ሰዎች አሉ። ስለዚህ ጀነራል ተሾመ… እያሉ የኃይል ሚዛን ከዚህ ስለሄደ ነው፣ ጀነራል ሲወርድ ደግሞ የኃይል ሚዛን ከዛ ወደዚህ ስለሄደ ነው የሚሉ አሉ። አቶ ኃይለማርያም ከዚህ ስለሆነ ወደዚያ ይሄዳል። አቶ ደመቀ ከዚህ ስለሆኑ ወደዚህ ይሄዳሉ የሚሉ ወሬዎች መበርከታቸውን እንገነዘባለን። ያም ሆኖ አቶ መለስን’ኮ የጋምቤላ ሕዝቦች፣ የደቡብ ሕዝቦች፣ የትግራይ ሕዝብ፣ የኦሮሞ ሕዝብ፣ የአማራ ሕዝብ የሌሎችም ኢትዮጵያ ሕዝቦች አልፎ አፍሪካውያን ሳይቀሩ የእኛ መሪ ናቸው ብሎ ነው የተቀበላቸው። ስለዚህ ይህ ሕዝብ የሚፈልገው የመጣህበትን መሠረት አይደለም፣ የመጣህበትን ብሔር አይደለም። የምትሰራለትን ስራ ነው። ይህ ነገር ያልገባቸው ፖለቲከኞችና አዋቂ ነን የሚሉ ሰዎች ካሉ ችግሩ የእነሱ ነው። ኢህአዴግ እንደሆነ አቶ ኃይለማርያም ይሁን፣ አቶ ደመቀ፣ አቶ አዲሱ፣ አቶ አባዱላ ገመዳ ወዘተ አንድን ብሔር የሚወክሉ ሰዎች አይደሉም። በአመራር ቦታ የሚቀመጡ ሰዎች በሙሉ በስራ ክፍፍል አንድ ብሔር ላይ እንመደብ እንችላለን እንጂ አንድን ብሔር ብቻ የምንወክል ሰዎች አይደለንም። የመላው ኢትዮጵያውያንን ሕዝቦች፣ ሁሉንም ሃይማኖቶች፣ ሁሉንም ብሔሮች፣ ሁሉንም ጾታዎች፣ ሁሉንም የዕድሜ ክልል በአጠቃላይ አብዛኛውን ሕዝብ እንወክላለን ነው የምንለው።
ሰንደቅ፡– በቀጣይ ግንባሩ የውጪና የውስጥ ተፅዕኖዎችን በምን መልኩ ሊቋቋም ይችላል? በተለይም ከሰሞኑ የዓለም አቀፉ አበዳሪ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) የሀገሪቱ ጠቅላላ ሀብት ወደ ታላቁ የህደሴ ግድብ እየሄደ በመሆኑ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ እየተጎዳ በመሆኑ ግድቡን እንዲቆም የሚል አስተያየት ሰጥቷል። ቀደም ሲል ድርጅቱ ለኒዮሊብራሊዝም አስገዳጅ ሁኔታዎች እጅ እንደማይሰጥ አቶ መለስ በህይወት በነበሩበት ወቅት ግፊቱን በግል ክህሎታቸው ጭምር ሲቋቋሙ እንደነበር ይታወሳልና ይሄንን ግፊት በምን መልኩ ነው የምትቋቋሙት?
አቶ በረከት፡- በዚህ ረገድ አዲስ ነገር ፍለጋ የምንሄድበት ነገር የለንም። ባለፉት ሃያ አመታት እንደ ኢህአዴጎች በርካታ ግፊቶችን ስንቋቋም ቆይተናል። ባለፉት ሃያ ዓመታት ሀገራችንን ለመለወጥ ብዙ ሰርተናል። ብዙ መሠረት ጥለናል። በብዙ መስኮችም ለውጥ መጥቷል። በዋና ዋና ሴክተሮች ከአይ ኤም ኤፍ የዓለም ባንክ ምክር ውጪ ሄደን ነው የሰራነው። ለውጪ ባለሀብቶች የባንኩን ዘርፍ ፍቀዱ ሲሉን አንፈቅድም ስንል፣ ቴሌኮሙኒኬሽንን ወደ ግል አዙሩ ሲሉን አይሆንም ስንል፣ መንግስት ከፋይናንስ ሴክተር እጁን ማንሳት አለበት ሲሉ እምቢ ስንል፣ የወለድ ምጣኔ በጣም ከፍተኛ ይሁን ሲሉን ለልማት በሚበጅ መንገድ ነው የምንወሰነው ስንል በአጠቃላይ ከነርሱ ጋር እየተፋለምን ነው የቀጠልነው። ከዚህም በኋላ አዲስ የሚመጣ ተፅዕኖ የለም። ካለም የእነሱንም ተፅዕኖ ለመቋቋም አዲስ የምንዘይደው መላ የለም። በአቶ መለስ ዘመን የነበረውን ሁሉንም ነገር የማስቀጠል ጉዳይ ነው። ልምዱን አግኝተናል። ዛሬ ኢትዮጵያ ማንም መጥቶ እጁዋን የሚጠመዝዝበት ደረጃ ላይ አይደለችም። በጣም ረጅም ርቀት ሄዳለች። በ1983 እና በ1984 ዓ.ም ያልተንበረከከ ሀገርና መንግስት ዛሬ ይንበረከካል ብሎ የሚጠብቅ አካል ካለ ይሄንን ሀገርና የህዝቡን ቁርጠኝነት ያልተገነዘበ ብለን ነው የምንወስደው።
ሰንደቅ፡- ኢህአዴግ ከአመራር ምርጫው በኋላ ለተቃዋሚዎች በጋራ ለመስራት ባስተላለፈው መልዕክት “በጋራ ምክር ቤት ለሚሳተፉ” ብሎ ለይቶ ነው መልዕክቱን ያስተላለፈው። በዚህ ረገድ መድረክን ጨምሮ ሌሎችን ፓርቲዎች ለማሳተፍ አዲስ የቀየሳችሁት አካሄድ አለ? በተለይም ከመድረክ ጋር አብሮ ለመስራት?
አቶ በረከት፡- አዲስ የምንከተለው ነገር የለንም። ከዚህ ቀደም ያስቀመጥናቸው ብዙ ግልፅ የሆኑ ነገሮች አሉ። መድረክ ከእኛ ጋር የነበረውን ድርድር ሲያፋርስ ነው የኖረው። ቁም ነገር ያለው ድርጅት ነው ብለን የምንወስድ ከሆነ በአንድ ዓለም አቀፍ ደረጃ ባለው ስነ-ምግባር መስማማት አለብን። መድረክ ሲያሰኘው አመፅ እየጫረ፤ ሲያሰኘው ደግሞ ጉልበት እጠቀማለሁ እያለ መቀጠል አይችልም። እኛም ለዚህ ኃይል ጫና እየተንበረከክን ልንሄድ አንችልም፤ ሕግና ስርዓት ያለበት ሀገር እንደመሆኑ መጠን ቢያንስ እንደ ፓርቲ ጤናማ መንገድ መከተሉን
መረጋገጥ አለበት። ነገር ግን እስከ ዛሬ ይሄ ድርጅት ጤናማ መንገድ ላይ መሆኑን አላረጋገጠም። ስለዚህ የድርድር ኳሱ ያለው በኢህአዴግ ሳይሆን በመድረክ ሜዳ ነው። በመሆኑም መድረክ ራሱን አስተካክሎ ከመጣ ለሁሉም የሚደረገው ይደረጋል። ነገር ግን አመፅን በግማሽ ልቡ እየተመኘና እየሰበከ እንቻቻል ቢል አያስኬድም። መድረክ ለመቻቻል ቅድመ ሁኔታን ሊያሟላ በሚችል ፖለቲካዊ ሁኔታ ላይ አይደለም ያለው።
ሰንደቅ፡– ኢትዮጵያ አሁን ከገጠማት ጊዜያዊ ችግር አንፃር ከኤርትራ መንግስት በኩል የሚደርስ የፖለቲካና የደህንነት ተፅዕኖ ይኖራል ተብሎ ይገመታል?
አቶ በረከት፡– የኤርትራ መንግስት ትንንሽ የመንደር ክፋቶችን ይሰራል። አቅሙም በዛ ደረጃ የተወሰነ ነው። የመንደር ክፋት የሚሰራን አካል የመንደር ክፋት ሰርቶ ጉዳት እንዳያደርስ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል። ከዚህ ያለፈ ግምት የሚሰጠው መንግስት አይደለም። እኛ የኤርትራን መንግስት ወደ መንደር ደረጃ የወረደ መንግስት አድርገን ነው የምናየው።

17 Responses to ““ህወሓት የታጋለው የህወሓትን ስርወ መንግስት ለመፍጠር ሳይሆን ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመፍጠር ነው” አቶ በረከት ስምኦን”

 1. Anonymous said

  I do not know why mass TPLF cyber babes commented , They knew the fact that
  Bereket is not Ethiopian,

 2. YON said

  WONDATA !! THE PERFECT MAN !! LONG LIVE ETHIOPIA !!

 3. Abraha said

  My appreciation, long live my country ETHIOPIA.

 4. September 21, 2012 at 10:44 AM

  Bereket always tell the truth. He is indispensable Ethiopia’s son. Long live to BEREKET.(He is “bereket” to EPRDF and to our Country. and I wish good time to our new PM H/mariam. finally I want comment on, Abraha Desta’s
  September 19, 2012 at 4:20 PM , “TPLF seems to introduce democracy after it has become weak.” TPLF have been never weak and will not be. If it is so it will be the weakness of the people because many are die for democracy. PM MELES dies does not mean the end of his vision and dream. it becomes the dreams and vision of every Ethiopian except few who are servant of outsiders.
  I am Tigrian I do not accept that I become weak as the result of MELES’s death rather I become strong, motivated and proud because the history of Ethiopia is changed, the vision of our heroes start to fulfill. we do not fight for power. we fight for equality. who ever the leader will be we only need peace, democracy, respect and development. If we face like the past challenges we always ready to fight for our freedom.
  Read history we never fight for power, we never be promote racism and also we wish to live peaceful life and scarify for that and we will be. ” QALSINA NEWIHN MERIRN AWETNA NAYGIDIN EYU” this sentence will always alive in every Tigrian BOLDLY and understood by every Ethiopian brothers and sisters.
  So what ever you say not competing for PM does not show weakness of TPLF rather the wise decision of the leaders. what do you thing which Tigrian gets what better than any Ethiopian as the result of TPLF’s leadership?
  PM Meles struggle for Africa as a whole. I also expect H/mariam will do same. LONG LIVE TO EPRDF.

  • Anonymous said

   I agreed about all you said except Appreciation’s on Breket…..if you do not mind can we have Ethiopia above EPRDF….IT IS JUST A PARTY…..LONG LIVE ETHIOPIA…

 5. Anonymous said

  Bereket always tell the truth. He is indispensable Ethiopia’s son. Long live to BEREKET.(He is “bereket” to EPRDF and to our Country. and I wish good time to our new PM H/mariam. finally I want comment on, Abraha Desta’s
  September 19, 2012 at 4:20 PM , “TPLF seems to introduce democracy after it has become weak.” TPLF have been never weak and will not be. If it is so it will be the weakness of the people because many are die for democracy. PM MELES dies does not mean the end of his vision and dream. it becomes the dreams and vision of every Ethiopian except few who are servant of outsiders.
  I am Tigrian I do not accept that I become weak as the result of MELES’s death rather I become strong, motivated and proud because the history of Ethiopia is changed, the vision of our heroes start to fulfill. we do not fight for power. we fight for equality. who ever the leader will be we only need peace, democracy, respect and development. If we face like the past challenges we always ready to fight for our freedom.
  Read history we never fight for power, we never be promote racism and also we wish to live peaceful life and scarify for that and we will be. ” QALSINA NEWIHN MERIRN AWETNA NAYGIDIN EYU” this sentence will always alive in every Tigrian BOLDLY and understood by every Ethiopian brothers and sisters.
  So what ever you say not competing for PM does not show weakness of TPLF rather the wise decision of the leaders. what do you thing which Tigrian gets what better than any Ethiopian as the result of TPLF’s leadership?
  PM Meles struggle for Africa as a whole. I also expect H/mariam will do same. LONG LIVE TO EPRDF.

 6. Anonymous said

  thank u bereket simon

 7. Elias said

  One of the toughest guy in EPRDF Bereket Simon….I appreciate his interview & EPRDF will continue its strength by its successors.

 8. Ethiopian said

  I like what he said about the Eritrean goverenment

 9. belay said

  Really I appreciate the comments and response of Ato Bereket Simon , he has briefly express the strategies and policies of EPRDF.

  • Anonymous said

   Belay, I am really sorry reading your disorganized and ungraamatical sentences about Bereket’s comments.I stongly advise to enhance your English laguage before you dare to write with it.Lear learn—so that you will be able to offer sound and logical comments.

 10. solomon said

  Really Mr.Bereket Simon You are one of the Greatest leader of EPRDF

 11. Anonymous said

  How guys make it a big deal to the drama of EPRDF?
  The issue of Ethiopians is not with the individuals of EPRDF members’ .it is with its policy, which is exclusive.
  The much told Secession is a change of people within same organization that rules Ethiopia over 21 years with iron fist policy.
  The people who are going to be supported by the old members are expected to do the same exclusive dogma, since they are baptized by the old members.
  So, what is new to blow a trumpet for hallow secession apart from a change of color?

 12. Haftu said

  AM VERY HAPPY,
  I PROUD BY THE DECISION OF TPLF AND EPRDF. REALLY AM VERY HAPPY
  LONG LIVE EPRDF

  • Abraha Desta said

   ! ……………….. On TPLF …………….. !

   1) Had there not been TPLF movement in Tigray (in the 17 years civil war), we would have not been noticed the coming of Dergue (government) soldiers to kill and belittle the people of Tigray. There would be no reason for the Dergue officials to deploy troops to the land of Tigray. (A police force would have been enough to protect the society). Then, there would be no mass atrocities. Dergue soldiers came to Tigray and killed us because there was a rebel group (TPLF); in order to destroy TPLF, they killed the innocent farmers. Now, there is no such mass killing in Tigray, because there is no an armed group (like TPLF) that struggles to control state power by force. Hence, there is a relative stability.

   2) Present-day, TPLF officials try to justify their rule by comparing their regime with that of the Dergue. Yet, such comparison is not legitimate. Because the Dergue never ruled Tigray (as TPLF is doing now). Tigray had been a war zone for 17 years where both TPLF and Dergue were trying to control the territory. Dergue seized state power in 1967 E.C and started to arrange the political structure so as to make the local government effective. In the SAME year (1967), TPLF began its armed struggle to ‘liberate’ Tigray. Most rural Tigray (known as ‘liberated areas of Tigray’ … hara meriet Tigray) was under TPLF. The Dergue’s rule was limited to urban areas. Finally, the war ended with the victory of TPLF. All in all, the Degue had no effective control over Tigray. So, the Dergue never ruled Tigray. TPLF should not compare itself with the era of the Dergue, because it difficult to enhance development efforts in a war time.

   3) I am happy that the Tigray farmers toppled the Dergue down, because it was not democratic. The Dergue was oppressive in that it wanted to rule by threatening us. The Tigray farmers used force (as a last resort) to remove the regime which did not allow peaceful opposition. Dergue was suppressive to all Ethiopians.

   4) The mission of the struggle of the Tigray farmers (I am not sure about the mission of the TPLF leadership) was not to control state power (They never struggled to replace one dictator by another dictator). The essence of the bitter struggle was to achieve freedom, democracy and development to all Ethiopians.

   5) Recently, Bereket Simon announced that TPLF‘s struggle was not to create a ‘dynasty’ but bring democracy. Yes, that is true. Yet, why now? Why such reforms after the death of Meles? Why after 21 years of oppressive rule? Why have Tigrians (and Ethiopians) been denied of freedom for the last 21 years? TPLF seems to introduce democracy after it has become weak. It can no longer be oppressive to Ethiopians, though it may continue its suppressive rule in Tigray. Anyways, the reforms being made are promising. Meles’ term of office was unlimited. Yet, now the term of officials is limited to two (10 years). The officials seem to revise (amned) their rigid constitution. This is a big step forward to the democratization of the government of Ethiopia.

   It is so!!!

   • Anonymous said

    Peopel do you know HISTORY?I gusse no!During TPLF straggle in Tigray Tplf fight first for them self b/c they were the one was oppressed and mistreated for who they are by the goverment.Then for the dimocracy of Ethiopia.I remember growing up in addiss being the Tention between Tigrean and the goverment.Because honestly Tigrayens are brave and also a noble peopel who work hard ,help each other and will do and thing if some one wants to tell them they are not good enough.Which it start all the fight.During Janhoy time he purpursely will put student after they graduarte high school to a teaching faculity,agrigulture and so on and so on but not politics,low or that kind of profession.Because they know the whole civilization,ruling class started in Tigray and if the peopel will learn politics,low….they will be in Leadership and they will be a treat to the Amharan clan which they claim is the destiny of Salamon(Minilik,can you see him being a decentent of Salamon).Any way they went and start to fight which eventualy throught the goverment and took the power.As far i know the TPLF goal is for equal right of the peopel.No one is better than any other Ethnic.We have our semilarity and minor differonse of cultural which is the beauty of Ethiopia.And they will do any thing to keep the peace we are enjoying now in Ethiopia.I know that and all I will say is BRAVO to TPLF!!!!long live!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: