Ethio Tribune

Plural News and Analysis on Ethiopia and HOA

 • RSS google news

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS Capital

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS Unknown Feed

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS Unknown Feed

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS Walta

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS DireTube Video

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • Enter your email address to receive notifications of new posts

  Join 481 other followers

 • Meta

 • Articles

 • ምስለ መለስ፡ የማንነቱ ገፅታ

  ምስለ መለስ፡ የማንነቱ ገፅታ

 • Live streaming

 • ETV live streaming
 • RSS Sudan Tribune

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS East Africa News

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS BBC News

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS Aljazeera

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS Climate Change News

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS Technology News

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • Archives

 • Flickr Photos: Ethiopia

ከመለስ እና ከጋናው ፕሬዚዳንት ሞት ጀርባ ድብቅ ምስጢር ይኖር ይሆን?

Posted by Ethio Tribune on August 25, 2012

meles-ena-gana(ሰንደቅ ጋዜጣ) በግንቦት ወር 2004 ዓ.ም መጀመሪያ በአሜሪካ ሜሪላንድ በካምፕዴቪድ በተካሄደው የስምንቱ የበለፀጉ የዓለም አገራት ስብሰባ ላይ ተጋብዘው ከተገኙት መሪዎች መካከል የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እና የጋናው አቻቸው ፕሮፌሰር ጆን ኢቫንስ አታሚልስ ይጠቀሳሉ። እነዚህ የአፍሪካ ገናና መሪዎች ከካምፕዴቪድ ስብሰባ ወደአገር ቤት ከተመለሱ በኋላ ግን የጤናቸው ሁኔታ አነጋጋሪ እየሆነ መምጣቱን ሰንደቅ ጋዜጣ ዘገበ።
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ መታመማቸው በተለያዩ ድረገጾች የሕዝብ መነጋገሪያ ርዕሰ ጉዳይ የሆነው ከካምፕዴቪድ በተመለሱ ሰሞን ነው። የመታመማቸው ዜና በማኅበራዊ ድረገጾች፣ በዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ሲቦካ፣ ሲጋገር ቆይቶ እጅግ ከረፈደ በኋላ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት መታመማቸውን በይፋ በማመን ሕክምናቸውን ተከታትለው በእረፍት ላይ መሆናቸውን፣ በቅርቡም ወደሥራ እንደሚመለሱ ሐምሌ 12 ቀን 2004 ዓ.ም በሚኒስትር አቶ በረከት ስምኦን አማካይነት ተገልጿል። እንደ ኢሳት ያሉ መገናኛ ብዙሃን እና አንዳንድ በውጪ አገር ያሉ ተቃዋሚ ኃይሎች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞተዋል በሚል ያሰራጩትን መረጃ አቶ በረከት ስምኦን “የበሬ ወለደ ወሬ ነው” በሚል ማስተባበላቸው የሚታወስ ነው። ይህም ሆኖ አቶ መለስ ከትናንት በስቲያ ከምሽቱ 5፡40 ሰዓት ገደማ ህይወታቸው ማለፉን የሚኒስትሮች ም/ቤት ትናንት ማለዳ ይፋ አድርጓል። ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ፤ ዜና ዕረፍት በኋላ በተለይ የአሟሟታቸው ሁኔታ ከጋናው ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጆን ኢቫንስ ጋር የሚያመሳስለው ነገር መታየቱና ለሕልፈተ ሕይወት የበቁበት ጊዜያትም የአንድ ወር ጊዜ እንኳን ልዩነት የሌለው የመሆኑ ጉዳይ ሌላ አነጋጋሪ አጀንዳ ሆኖ ብቅ ብሏል።
አቶ መለስ እና ፕሮፌሰር ጆን ኢቫንስ አሟሟት መመሳሰል
የጋናው ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጆን ኢቫንስ በ68 ዓመታቸው በድንገት ሞታቸው የተሰማው ማክሰኞ ሐምሌ 17 ቀን 2004 ዓ.ም (ጁላይ 27/2012) ነው። ፕሬዚዳንቱ በሕመማቸው ወቅት ተገቢውንና በቂ ሕክምና አግኝተዋል ተብሎ በጋና ሕዝብ አይታመንም። ሕዝቡ ከቀብራቸው በፊት በምን ሕመም እና እንዴት እንደሞቱ በቂ መረጃ ለማግኘት ፍላጎት ቢኖረውም፤ ነገሩ በሚስጢር በመያዙ ከመላምት ያለፈ ነገር ማግኘት አልቻለም። የጋና ሕክምና ማኅበር የፕሬዚዳንቱ አሟሟት እንዲጣራ ለአዲሱ ፕሬዝዳንት ጆን ድራማኒ ማሃማ ጥያቄ አቅርቦ አዎንታዊ ምላሽ አላገኘም። ሕዝብ ይፋ መረጃ እየጠየቀ ባለበት ሰዓት አዲሱ ፕሬዝዳንት ቃለመሃላ ፈፅመው ወደመደበኛ ሥራቸው ገብተዋል። በዚህም ምክንያት የጋና ሕክምና ማኅበር የቀድሞው ፕሬዝዳንታቸው አሟሟት በምርመራ ካልተረጋገጠ እንቅልፍ እንደማይወስዳቸው እስከመናገር መድረሳቸውን የተለያዩ የዜና ምንጮች ዘገባ ያሳያል።
ዶ/ር ባይሾፕ ዳግ ሃርዋርድ ሚሊስ የተባሉ ፖስተር “ለጋና ሕዝብ የፕሬዚዳንቱ ሞት በተለየ መልኩ እየተሸጠ ነው። እንደማስበው ለሕዝብ የተዛባ መረጃ መስጠት አስፈላጊ አይደለም። ሁላችንም ሰብዓዊ ፍጡሮች ነን። ሕመም የማንም ስህተት አይደለም” ሲሉ በመንግሥታቸው ላይ የተሰማቸውን ቅሬታ ገልፀዋል።
ፕሬዝዳንት ጆን ኢቫንስ የሞቱት “በስትሮክ” ነው የሚሉ ይፋዊ ማረጋገጫ ያላገኙ መረጃዎች በአንድ በኩል ሲናፈሱ በሌላ በኩል፤ የሞታቸው መንስኤ “ካንሰር” መሆኑን የሚዘግቡ ነበሩ። የቀድሞው የአገሪቱ መሪ ጄሪ ሮውሊንግ ፕሬዚዳንቱ የሞቱት በጉሮሮ ካንሰር ነው ሲሉ የፕሬዚዳንቱ ወንድም በበኩላቸው በስትሮክ ነው በማለት የማይገናኙ ኀሳቦችን መስጠታቸው ሕዝቡን ብዥታ ውስጥ ከቶታል።
የ57 ዓመቱ ጎልማሳ የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ መታመም ከሟቹ የጋና ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጆን ኢቫንስ አታሚልስ ጋር የሚመሳሰልባቸው ጉዳዮች ይታያሉ። የመጀመሪያውና ቀዳሚው በካምፕዴቪዱ የበለፀጉ አገራት ስብሰባ ላይ ጎን ለጎን ተቀምጠው ኀሳባቸውን ሰጥተው ከተመለሱ በኋላ ሁለቱም መሪዎች የመታመማቸውና ተከታትለው የመሞታቸው ሚስጢር ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት የጠ/ሚኒስትሩን መታመም በማኅበራዊ ድረገጾች በየዕለቱ ኡኡ ሲባል “ወሬው የበሬ ወለደ ነው” ከማለት ባለፈ ማረጋገጫ ሳይሰጥ በሚስጢር ይዞት ቆይቷል። ከወራት ቆይታ በኋላ ሕዝብ አስቀድሞ ያወቀውን ዜና በመንግሥት ማረጋገጫ ተሰጥቶታል።
አቶ መለስ ዜናዊ ከመሞታቸው አስቀድሞ ስለሕመማቸው ሁኔታ፣ ሕክምና ስለሚከታተሉበት ሆስፒታል ዝርዝር ማብራሪያ የኢትዮጵያ መንግሥት አልሰጠም። ከዜና እረፍታቸው በኋላም በትናንትናው ዕለት ስለሕመማቸው መንሰኤ የተጠየቁት አቶ በረከት ሰምኦን እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል። የሚኒስትሮች ም/ቤት ግን ትናንት ማለዳ የጠ/ሚኒስትሩን ሞት ይፋ ባደረገበት መግለጫው ላለፉት ሁለት ዓመታት ያማቸው እንደነበር በድፍኑ ፍንጭ ሰጥቷል።
ይህም ሆኖ ግን ማኅበራዊ ድረገጾች ከተለያዩ ምንጮች አገኘን ያሉትን መረጃ በመያዝ የጠ/ሚኒስትር መለስ የሕመም መንስኤ ካንሰር መሆኑን በተደጋጋሚ ፅፈዋል። አንዳንዶች ስትሮክ መሆኑን ይዘግቡ እንጂ፤ ወሬዎቹ ከመንግሥት ወገን ይፋዊ ማረጋገጫ እስካሁን አላገኙም። ኢትዮጵያዊያንም የጠ/ሚኒስትራቸው የሞት መንሰኤ በይፋ እንዲገለፅ በተለያየ መንገድ በመወትወት ላይ ናቸው።
ከካምፕዴቪድ ስብሰባ መልስ የሁለቱ አንጋፋ መሪዎች ሕልፈተ ሕይወት አጋጣሚ ይሁን ወይስ የታቀደበት የሚለው የሚስጢር ቋጠሮ አሁንም አልተፈታም። በርግጥም ከመሪዎቹ ሞት ጀርባ አንዳች ሚስጢር ይኖር ይሆን? ወደፊት ጊዜ የሚፈታው ይሆናል ሲል ሰንደቅ ጋዜጣ ዘገባውን ቋጭቷል።

One Response to “ከመለስ እና ከጋናው ፕሬዚዳንት ሞት ጀርባ ድብቅ ምስጢር ይኖር ይሆን?”

 1. Tadele teklu said

  Yemeles mot be asdenegxnm kxelat yixbken

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: