Ethio Tribune

Plural News and Analysis on Ethiopia and HOA

 • RSS google news

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS Capital

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS Unknown Feed

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS Unknown Feed

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS Walta

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS DireTube Video

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • Enter your email address to receive notifications of new posts

  Join 481 other followers

 • Meta

 • Articles

 • ምስለ መለስ፡ የማንነቱ ገፅታ

  ምስለ መለስ፡ የማንነቱ ገፅታ

 • Live streaming

 • ETV live streaming
 • RSS Sudan Tribune

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS East Africa News

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS BBC News

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS Aljazeera

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS Climate Change News

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS Technology News

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • Archives

 • Flickr Photos: Ethiopia

“ሙስሊም ወንድማማቾች የፖለቲካ ፓርቲ” ለመመስረት ጥያቄ መቅረቡ ተሰማ

Posted by Ethio Tribune on July 25, 2012

 • መንግስት በጥያቄው ደንግጧል
 •    “ ማንኛውም ሰው ለማንኛውም ዓላማ በማህበር የመደራጀት መብት አለው ፡፡” የኢትዮጵያ ህገ መንገስት አንቀጽ 31
(አንድ አድርገን ሐምሌ 18 2004 ዓ.ም)፡- የሀገሬ ሰው “የባሰ አለና ሀገርህን አትልቀቅ” ይላል ፤  በአሁኑ ሰዓት  እንዲህማ አይታሰብብ የምንለው ጉዳይ እንደ ትልቅ ጉዳይ ብቅ ብሏል ፤ ይህ ጥያቄ ውስጠ ወይራ ነው ፤ መንግስት የሚደሰኩርለትን ዲሞክራሲን መሰረት አድርጎ የውስጥን አላማ ለማሳካት የተነሳ ጥያቄ ፤ ካለመጠይቅ ደጃዝማችነት ይቀራል በማለት የተነሳ ወቅታዊ ጥያቄ ፤ ሙስሊሙን ነጻ አወጣለው በማለት የሙስሊምን የበላይነት ለማረጋገጥ ሲባል የዘመናት ጥያቄዎቻውን ለመመለስ ያመቻቸው ዘንድ የጠየቁት ጥያቄ ፤ ……
የዛሬ ሁለት ዓመት ገደማ ተሰናባቹ የአሜሪካ የአዲስ አበባ አምባሳደር በጊዜው  ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ስለሚደረገው ሰርጎ ገብ ውሀቢዝም እንቅስቃሴ ከዊኪሊክስ የተገኝ መረጃ ለዓለም ወጥቶ ነበር ፤ ይህን መረጃ ከአዲስ አበባ ወደ ዋሽንግተን ከመላኩ በፊት የኢህአዴግ መንግስት ጠንቅቆ እንደሚያውቀው በጊዜው በሚወጡ ማስረጃዎች ለማወቅ ተችሏል ፤ የአሜሪካ ኢምባሲ ተቀማጭነቱ አዲስ አበባ የሆነው መስሪያ ቤት በኢትዮጵያ ወደፊት ወሀቢያ የእግር እሳት እንደሚሆንባት ጨምሮም ገልጾ ነበር ፤  የዛሬ ሁለት ዓመት በደሴ ፤ በአርሲ ፤ በሀረር ፤ በምስራቅ ሀረርጌ እና በበርካታ የሀገሪቱ ክፍሎች ወሀቢያን የሚያራምዱ ሰዎች የራሳቸው በሚሏቸው ሰዎች አማካኝነት ረብጣ የነዳጅ ብር እየከፈሏቸው አመለካከታቸውንና አይዲዎሎጂያቸውን ወደ ሙስሊሙ ማህበረሰብ የማውረድ ስራ ሲሰሩ እንደነበር ይታወቃል ፤ከዊኪሊክስ የወጣ መረጃን ለማንበብ ይህን ይጫኑ Wahabism in Ethiopia as “CULTURAL IMPERIALISM”) 
ይህ አካሄድ መጨረሻው ኢስላማዊ መንግስት እስከ ማቋቋም ይደርሳል ፤ እኛ ይህን ለማለት የደፈርነው በጊዜው ከወጡ ሁለት መረጃዎች በመነሳት እንጂ መንግስት በኢቲቪ የሚደሰኩረውን ነገር መሰረት አድርገን አይደለም ፤ በመሰረቱ ኢቲቪ ላይ በአሁኑ ወቅት እያየን ያለነው ሁሉም እውነት አይደለም ሁሉም ደግሞ ውሸት አይደለም ፤ የፖለቲካ አካሄድ እንዳለ ሆነ በርካታ እውነታዎችም አብረውት እንዳሉት ለማየት ችለናል ፤ መንግስት ይህ ስር የሰደደ ለሀገርም ይሁን ለህዝብ የማይጠቅምን ፤ ሀገርን አደጋ ላይ የሚጥልን አመለካከት በጊዜው እንደ ተራ ነገር በመመልከት በ2003 ዓ.ም የካቲት ወር የሚመለከታቸውን የእስልምና የእምነቱን አባቶች በመጥራት በሀገሪቱ የሚካሄደውን ነገር እንደደረሰበት እና እጃቸውን እዚህ ላይ የሰደዱ ሰዎች እጃቸውን ከዚህ አመለካከት ላይ እንዲያነሱ ያለበለዚያ ግን ህጉ በሚፈቅደው መጠን እርምጃ እንደሚወስድ አበክሮ መናገሩ ይታወቃል ፤   ነገር ግን መንግስት የተናገረውን ወደ ተግባር ሲለውጠው መመልከት አልቻልንም ፤ ይህ አመለካከት ሲጀምር ግብር በሚከፈልበት ቦታ ላይ ሙስሊም ማህበረሰብ እንዳይሰግድ ያዛል ፤ ኢትዮጵያ የአረብ ሀገራት አባል እንድትሆን ጠንክሮ ይሰራል ፤ ሙስሊም ነጋዴ ግብር መክፈል ያለበት ለእስልምና መንግስት እንጂ ለማንም እንዳልሆነ አበክሮ ያሰብካል ፤ ሀገሪቱ በሸሪአ ህግ  እንድትተዳደር ይደነግጋል ፤ ወሃቢያን ለማስፋፋት ፍቃደኛ ለሆነ ሰው ለአንድ ተራ ምዕመንም በወር ከ10 ሺህ ብር በላይ በካሽ እንደሚከፍለው መረጃዎች ያመለክታሉ ፤
መጀመሪያ የታሰበውና የተነሱበትን አላማ ማሳካት ያስችላቸው ዘንድ በአገሪቱ ላይ ሙስሊሞችን የሚወክል ፤ ሙስሊሞችን ነጻ ለማውጣት የሚታትር የፖለቲካ ፓርቲ ለማቋቋም ፍቃድ መጠየቃቸው በአሁኑ ወቅት ተሰምቷል ፤ ይህ ጥያቄ መቅረብ ማንንም ሳይሆን የመንግስት ባለስልጣናትን ክፉኛ አስደንግጧቸዋል ፤ ሰዎቹ ይህን ጥያቄ ሊያነሱ የፈለጉበት ነጥብ ምንድነው ?  ጥያቄው መነሳቱ ሳይሆን ትልቁ ጥያቄ ሊሆን የሚችለው አሁን የያዙት አመለካከት ምን ያህል ረዥም ርቀት ለመጓዝ ቆርጠው መነሳታቸው ጭምር ነው ፤ ይህ የፖለቲካ ፓርቲ መተዳደሪያ ደንቡ ምን ሊሆን ይችላል ?  አባላቶቻቸው እነማን ናቸው ? ምን አይነት አላማ ለማሳካት ነው በፖለቲካ ፓርቲነት መቋቋም ያስፈለጋቸው ? ይህ ሊመለስ የሚገባው ጥያቄ ነው ፡፡ ይህ ወሬ የተሰማው በአሁኑ ሰዓት ሀገሪቱ ያለችበትን የሃይማኖት ችግር እንዴት እዚህ ደረጃ ላይ እንደደረሰ ፤ ከእምነት ተቋማት ምን አይነት ጥያቄዎች ለመንግስት አካላት እንዳቀረቡ ፤ ጥያቄዎች ከህገመንግስቱ አኳያ እንዴት እንደሚታዩ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በሚወያዩበት ወቅት የተነሳ ሃሳብ ነው ፤
በአሁኑ ሰዓት ተሀድሶያውያንን ለመጠራረግና ከቤተክርስቲያን ውስጥ ለማስወጣት ከፍተኛ ስራ ተሰርቷል ፤ በዚህ አጋጣሚ ብዙዎች ለምን እንዲወጡ ትገፏችዋላችሁ? ለምን ተምረው አይመለሱም ይላሉ?  ሰዎቹ የእውቀት ችግር የለባቸውም ፤ “አውቆ የተኛ ቢቀሰቅሱት አይሰማም” ነው ብሂሉ ፤ ይህ የውስጥ ችግር ሲሆን ይህን የመሰለ የውጭ ችግርን ለመከላከል ምን እየሰራን እንገኛለን ? እኛ እንደሚታየን ይህም የወደፊት የቤተክርስቲያን አደጋ ነው ፤ ዛሬ ዘሩን ለመዝራት ሲሞክሩ ብንመለከት ነገ ፍሬ አፍርቶ የምናጭድበት ጊዜ እንደማይመጣ እርግጠኞች ሆነን መናገር አንችልም ፤ አይኖቻችንን ረዥም ርቀት እንዲያዩ እንፍቀድላቸው ፤
ይህን የመሰለ ፓርቲ ስያሜ የምናገኝው በግብጽ ፤ በሊቢያ ፤ በቱኒዚያ ባህሪን በሶሪያ እና መሰል የአረብ ሀገራት ነው ፤ በግብጽ 90 በመቶ የሚሆነው የእስልምና ተከታይ ሲሆን ቀሪው 10 በመቶ ደግሞ የክርስትና ተከታይ መሆኑ ይታወቃል ፤ ባህሬን ውስጥ ካላት 1.2 ሚሊየን ህዝብ ውስጥ 98 በመቶ የሚሆነው የእስልምና እምነት ተከታይ ሲሆን የተቀሩት ደግሞ የተለያዩ እምነቶችን ይከተላሉ ፤ በተመሳሳይ ኳታር 1.7 ሚሊየን ከሚሆነው ህዝቧ አብዛኛው የእስልምና እምነት ተከታይ ነው ፤ በሶሪያ 89 በመቶ የሚሆነው ሙስሊም ሲሆን 11 በመቶ ግድም የሮማን ካቶሊክና ክርስትያኖች እንደሆኑ መረጃዎች ያመለክታሉ ፤ ይህን ነገር ያነሳነው ያለምክንያት አይደለም ፤ እነዚህ ሀገራት ላይ ሙስሊም ወንድማማቾች የፖለቲካ ፓርቲ ለማቋቋም ጥያቄ ቢነሳ ተገቢ ነው ብለን መቀበል እንችል ይሆናል ፤ መጀመሪያውኑ ህገ መንግስታቸው የሸሪያን ህግ መሰረት አድርገው ስለመሰረቱት የፓርቲውን ምስረታ ለመፍቀድ ብዙም አዳጋች አይሆንባቸውም የሚል ግምት አለን ፤ እንደ ኢትዮጵያ ባለች ከ45 በመቶ በላይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስትያኖች፤ 33 በመቶ ሙስሊም አማኞች ፤ 18 በመቶ አካባቢ ፕሮቴስታንቶች በሚኖሩበት ሃገር ላይ ይህን ጥያቄ ማቅረብ ማለት ምን ማለት ነው ?
የኢትዮጵያ ህገ መንግስት በአንቀጽ 11 “የመንግስትና የሃይማኖት መለያየት” በሚል በንኡስ አንቀጽ 1 ላይ “መንግስትና ሃይማኖት የተለያዩ ናቸው” ይላል ፤ በንኡስ አንቀጽ 2 ላይ “መንግስታዊ ሃይማኖት አይኖርም” በማለት ያክላል ፤ በስተመጨረሻም በንኡስ አንቀጽ 3 ላይ “ መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም ፤ ሃይማኖትም በመንግስት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም” በማለት በግልጽ ያስቀምጣል ፡፡ ይህን አንቀጽ እንደ አንቀጽ ከመቀመጡ በተጨማሪ መንግስት የእምነት ተቋማት እና ተከታዮቻቸው በዚህ አንቀጽ ላይ መብታቸው ምን ድረስ ነው ? ግዴታቸውስ ? የሚለውን ጉዳይ በአግባቡ የማስተማር እና የመተርጎም ስራ የሰራ አይመስለንም ፤ በህገ መንግስቱ አንቀፅ 27 ንኡስ አንቀጽ 2 ላይ “ የሃይማት ተከታዮች ሃይማታቸውን ለማስፋፋትና ለማደራጀት የሚያስችሏቸውን የሃይማት የትምህርትና የአስተዳደር ተቋማትን ማቋቋም ይችላሉ” በማት ያስቀምጣል ፤ ይህ አንቀጽ እንደሚነግረን “የሃይማት የትምህርትና የአስተዳደር” ተቋማትን እንጂ የፖለቲካ ተቋም አይልም ፤  ህገ መንገስቱ አንቀጽ 31  ላይ “ ማንኛውም ሰው ለማንኛውም ዓላማ በማህበር የመደራጀት መብት አለው ፡፡ ሆኖም አግባብ ያለውን ህግ በመጣስ ወይም ህገ መንግስታዊ ስርአቱን በህገወጥ መንገድ ለማፍረስ ተመሰረቱ ወይም የተጠቀሱትን ተግባራት የሚያራምዱ ድርጅቶች የተከለከሉ ይሆናሉ” በማለት ያስቀምጣል ፤ እዚህ አንቀጽ ላይ “ለማንኛውም ዓላማ በማህበር የመደራጀት መብት አለው ” ማለት ሁሉንም ስለሚያካትት ለምን ሙስሊም ወንድማማቾች የፖለቲካ ፓርቲን ለመመስረት ጥያቄ አቀረቡ ማለት   አይቻልም ፤ ለምን ቢባል ህገመንግስቱ ለማንኛውም አላማ በማህበር የመደራጀት መብትን ስለሚፈቅድ ፤ ሙሉ ህገ መንግስቱን ቢያነቡት አንድም ቦታ ሃይማኖትን መሰረት አድርጎ ስለሚቋቋም የፖለቲካ ፓርቲ የሚለው ነጥብ የለውም ፤ ይህ ለጥያቄያቸው ክፍተት የሰጣቸው ይመስለናል ፤ የህጎች ሁሉ የበላይ ደግሞ ህገመንግስቱ ነው፡፡
ስህተቶች የሚፈጠሩት አንድም ባለማወቅ ሲሆን ሁለተኛ ደግሞ የተቀመጠውን ነገር በአግባቡ ከመተርጎም ጋር በተያያዘ ችግር ወይም ህጉን ክፍተት በመጠቀም የሚደረግ የህግ ትርጓሜ  ሊሆን ይችላል ፤ ምንም ይሁን ምን ይህን ጥያቄ እንደ ተለያዩ የአረብ ሃገራት በሀገራችንም ፓርቲውን ለማቋቋም የሚፈልጉ ሰዎች ተነስተዋል ፤ በመሰረቱ ይህ አደጋው መጀመሪያ ለማን እንደሆነ ሳይታለም የተፈታ ጉዳይ ነው ፤ ጥያቄውን የተቀበለው አካል በመጀመሪያ ያስብበት ፤ እኛ ግን ሁለተኛ ተጎጂም መሆን ስለሌለብን የሚመለከቱንን ነገሮችን ብቻ አጽንኦት ሰጥተን ብንከታተላቸው መልካም ነው የሚል ሃሳብ አለን ፡፡ እኛ የሆነውንና የተደረገውን ለእናንተ ለአንባቢያን አድርሰናል ፤ ይህን ጥያቄ  እርስዎ እንዴት ይመለከቱታል ? ሃሳብዎትን ያካፍሉን……

በሀይማኖት፣ በብሔር፣ በዘር ፣ በቋንቋ ተጠራርቶ የሚመሰረት የፖለቲካ ፓርቲ ለሀገራችን አንዳች የሚያመጣው ሰላም አይኖርም፡

(source: http://www.andadirgen.blogspot.de/2012/07/blog-post_24.html)

5 Responses to ““ሙስሊም ወንድማማቾች የፖለቲካ ፓርቲ” ለመመስረት ጥያቄ መቅረቡ ተሰማ”

 1. Anonymous said

  ይህ ወያኔ ሙስሊሙንና ክርስቲያኑን ሊያጋጭ ያመጣው ተራ አሉባልታ ነው፡፡
  ከአሁን ቡሀላ የኢትዮጲያውያን ንቃተ ህሊና ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን አውቃችሁ ተራ አሉባልታችሁ ብትተዉት ጥሩ ነው፡፡ እኛ ኢትዮጲያውያን ነቅተናል፡፡ እኛን እያባላችሁ እናንተ ስልጣናችሁን ታሞቃላችሁ፡፡ በአሁኑ ሰዓት ወያኔ የሞት ሽረት ትግል እያደረገ እንደሆነ እናውቃለን፡፡
  ሁሉም ዉሸት ነዉ አንድም እዉነት የለዉም …አሁን ክርስቲያኑም ሙስሊሙም ነቅቶአል ሸወድኩ ስትል ተሸዉደሀል

 2. Anonymous said

  እኔ ያልገባኝ የእስላም መንግስት የሚፈልግ ሰዉ ግን አለ? ካለም እብድ ነዉ መንግስት በራሱ ወጭ ሙሉ ህክምና ያድርግለት መቼም ዜጋ ነዉና: ሙስሊሙ ሁሉም ክርስትናን ተቀብለናል ቢል ወይም ክርስቲያኑ ሁሉም እስልምናን ተቀብለናል ቢሉ መንግስት ምን ይላል? በርግጠኝነት አሸባሪዎች ህገ መንግስት ለመናድ ነዉ የፈለጉት ይለናል:ሀይማኖትን መምረጥ ቀረ :መንግስት ችግሮችን ቶሎ ካልፈታ ኑሮ የተወደደበት ሁሉ ሊፈነቅሉት ነዉ

 3. Anonymous said

 4. a said

  ይህ ወያኔ ሙስሊሙንና ክርስቲያኑን ሊያጋጭ ያመጣው ተራ አሉባልታ ነው፡፡
  ከአሁን ቡሀላ የኢትዮጲያውያን ንቃተ ህሊና ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን አውቃችሁ ተራ አሉባልታችሁ ብትተዉት ጥሩ ነው፡፡ እኛ ኢትዮጲያውያን ነቅተናል፡፡ እኛን እያባላችሁ እናንተ ስልጣናችሁን ታሞቃላችሁ፡፡ በአሁኑ ሰዓት ወያኔ የሞት ሽረት ትግል እያደረገ እንደሆነ እናውቃለን፡፡

 5. Umex said

  ከ3 ጥያቄዎች ሌላ ተጨማሪ ጥያቄ ለመንግስት አላነሳንም::” በሀይማኖት ሽፉን አንዳችም ድብቅ አላማ የለንም:: ይህንን ሁሉም ኢትዮጲያዊ ሊያዉቀዉ ይገባል:: በመንግስት ሚዲያዎች የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ስለተነዛ ሶስቱ ህገ መንግስታዊ ጥያቄዎቻችን ህገ ወጥ ሊሆኑ አይችሉም:: ህገ መንግስታዊ መብታችን ይከበርልን ነዉ ያልነዉ!! የሀገራችን ሰላም ከማንም በላይ ያሳስበናል::አላሁ ክበር

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: