Ethio Tribune

Plural News and Analysis on Ethiopia and HOA

 • RSS google news

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS Capital

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS Unknown Feed

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS Unknown Feed

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS Walta

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS DireTube Video

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • Enter your email address to receive notifications of new posts

  Join 481 other followers

 • Meta

 • Articles

 • ምስለ መለስ፡ የማንነቱ ገፅታ

  ምስለ መለስ፡ የማንነቱ ገፅታ

 • Live streaming

 • ETV live streaming
 • RSS Sudan Tribune

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS East Africa News

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS BBC News

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS Aljazeera

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS Climate Change News

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS Technology News

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • Archives

 • Flickr Photos: Ethiopia

የዲሲ(DC) ፖለቲከኞች የኋልዮሽ ጉዞ ታሪክ በጨረፍታ

Posted by Ethio Tribune on July 10, 2012

Highlight:

“የኢትዮጵያ ቅርስና ውርስ ማህበረሰብ በሰሜን ኣሜሪካ (EHSNA) የሚባል ድርጅት ኣቋቋሙ፡፡ ዝግጅቱን የሚያቀርብበት ጊዜም ከ ESFNA ጋር በተመሳሳይ ጊዜ እንዲሆን ወሰኑ፡፡ ብርቱካንም የዝግጅቱ እንግዳEthiopian diaspora እንድትሆን ኣደረጉ -ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ፡፡ እንዲህም ኣሉን – “የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ለዘመናት ስታቀርበውና ስትታገልለት የነበረውን የብርቱካን የክብር እንግዳነት ጉዳይ ይሄው እውነተኛና ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ኣሳክተውታል፡፡ ደስ ብሎናል ደስ ይበላችሁ፡፡ድል ለኛ ሞት ለ ESFNA” ኣሉ፡፡

የወያኔ ነው የተባለው ESFNAም ሃሳቡን ቀይሮ ብርቱካንን ጋበዘ፡፡ እንዲህ ነው ጨዋታ፡፡ “ታሪክ ራሱን ይደግማል” እንደሚባለው ዘንድሮ 2012 ደግሞ ሌላ “የመላ ኢትዮጵያውያን የስፖርት ማኅበር ኣንድ (AESAOne)” የሚባል ድርጅት ተቋቋመ፡፡

ይህ ኣጭር መጣጥፍ ዲሲ ላይ ስለመሸጉት ፖለቲከኞቻችን የህይወት ጉዞና የሰሞኑ እንቅስቃሴኣቸውን በተመለከተ የሚያማ ጽሁፍ ነው፡፡ ስለ ኢትዮጵያ ፖለቲከኞች መፃፍ ለሚፈልግ ሰው ስለ ዲሲ ፖለቲከኞች መፃፍን የመሰለ ኣዝናኝ ነገር እንደሌለ በዚህ ኣጋጣሚ ልነግረው እፈልጋለሁኝ – ኣያሌ ያልተነገሩ ታሪኮች ኣሏቸውና (ስለ ኢህኣዴግ ብዙ ተጽፏል)፡፡

እነዚህ ሰዎች ባለፉት 21 ኣመታት ኣቅጣጫና መድረሻ የሌለው ተቃውሞ ሲያሰሙ የከረሙ ናቸው፡፡ ኣብዛኞቹ በትርፍ ሰኣታቸው ኣንዳንዶቹ ደግሞ እንደ ሙሉ ጊዜ ስራ (ቢዚነስ) የያዙት ናቸው፡፡ እንደ ሙሉ ሰኣት ቢዝነስ ከያዙት ውስጥ ለምሳሌ ኣበበ በለው፣ ኣበበ ገላው፣ ኣበበ በላቸው፣ ኣበበ ተክሌ፣ ኣበበ ሃይሌና ሁሉም የኢሳት ሰራተኞች ይገኙባቸዋል፡፡

ተቃውሞኣቸው የጀመረው ገና ኢህኣዴግ ምን ኣይነት መንግስት እንደሚያቋቁም ሳያውቁ፣ ዴሞክራሲያዊ ነው ኣይደለም ሳይለዩ ብቻ ኢህኣዴግ የሚባል ድርጅት ስልጣን ስለያዘ ብቻ መቃወም የጀመሩ ናቸው፡፡ በባህርያቸው ብሄር ብሄረሰቦች፣ በኣፍ መፍቻ ቋንቋ መማር፣ የራስን እድል በራስ መወሰን፣ ኦሮሚያ ክልል፣ ሶማሌ ክልል፣ ትግራይ …… ወዘተ የመሳሰሉ ቃላቶች ኣይመቿቸዉም፡፡ ከ 1983 ዓ/ም ጀምሮ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ጥምረቶችን ኣቋቁመዋል፣ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰልፎችን ኣደራጅተዋል፣ በብዙ ሚልዮን የሚቆጠር ገንዘብ ከደጋፊ ኣሰባስበዋል፣ ኣልፎ ኣልፎም በስድስት ወርና በኣንድ ኣመት ውስጥ ኢህኣዴግን እንጥላለን ብለው ለደጋፊዎቻቸው ቃል ገብተው ባሉበት ጭጭ ብለዋል፡፡ ስለ ዛሬይቷ ኢትዮጵያ ሲኦልነት፣ ስለ ኢህኣዴግ ኣውሬነትና ስለ ኢህኣዴግ ደጋፊዎች ጭራቅነት ብዙ ሺ ኣርቲክሎችን ጽፈዋል፣ ኣሳትመዋል፡፡ ለበርካታ የኣሜሪካ ሴናተሮች በስልክ፣ በኢሜይል በደብዳቤ ኢትዮጵያ ላይ ማእቀብ እንዲጣል ኣቤቱታ ኣቅርበዋል፡፡ በኣንድ ወቅትም ወደ ኤርትራ ጎራ ብለው ኣቶ ኢሳያስን ተማፅነዋል፡፡ በርግጥም የዛሬን ኣያርገውና ከ 2000 ዓ/ም በፊት ዋሽንግተን ዲሲ ለኢህኣዴግ የማትመችና የማትደፈር ከተማ ኣድርገዋት ቆይተዋል (ኣሁን ስልታዊ ማፈግፈግ ኣድርገው ይሆን?)፡፡

የውድቀታቸው መጀመርያ በ1997 ዓ/ም ኢትዮጵያ ውስጥ የተደረገው በብዙዎቹ ዘንድ ነጻና ዲሞክራሲያዊ ነበር የተባለለት ምርጫ ነው፡፡ በወቅቱ እነዚህ የዋሽንግተን ፖለቲከኞች በኣንድ ሺ ኣመት ኣንዴ የማይገኝ እድል (Jackpot ) ከች ኣለላቸው – በምርጫ ተወዳድሮ ብዙ ወንበሮችን ባገኘው በቅንጅት በኩል ፓርላማ መግባትና በሂደት የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር መቀራረብና ሰላማዊና ስልጡን በሆነ መንገድ ማሳመን፡፡ ሆኖም ከመጀመርያው መቃወም እንጂ ሌላ ኣላማ ኣልነበራቸውምና እድሉን ሳይጠቀሙበት ቀሩ፡፡ ፓርላማ ኣንገባም የማለታቸው ጦስም ወደ ኣንድ ሺ ኣንድ መቶ ድርጅቶች ፣ጥምረቶችና ግለሰቦች በታትኗቸው ይሄው ኣሁን ያሉበት የኋልዮሽ ጋሪ ውስጥ ከቷቸዋል፡፡ (እዚህ ላይ RIP ብያለሁ)፡፡ በመሆኑም ባለፉት ጥቂት ኣመታት የተደራጀ የፖለቲካ ድርጅትና ኣላማ ኣጥተዋል፡፡ ደጋፊዎቻቸው ሁሉ ተሰላችቷል፡፡ ስለዚህ የሚደረጉ ተቃውሞዎች በሙሉ ያልተደራጁና ኣንዳንዶቹም ኣስቂኝ ናቸው – ለምሳሌ የህዳሴ ግድብን መቃወም፣ ቻይና ለኢትዮጵያ እርዳታ እንዳትሰጥ ባንዲራዋን ማቃጠል፣ የኢትዮጵያ መንግስት የተለያዩ ስብሰባዎችን ሲያደርግ ማወክና ኣጋጣሚው ከተመቻቸም የስብሰባው ተሳታፊዎቹን መደብደብ፣ ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያ ኣየር መንገድን እንዳይጠቀሙ መወትወት፣ መንግስትን የሚደግፉ ወይም ኢትዮጵያ ውስጥ መዋእለ ነዋይ ያፈሳሉ ብለው ያሰቧቸውን ሰዎች ስም ማጥፋት ወዘተ….. ናቸው፡፡

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ መንግስት ዋሽንግተን ዲሲን ከማትደፈር የተቃዋሚዎች ምሽግነት ወደ ትግል ሜዳነት ቀይሯታል፡፡ ባለፉት ጥቂት ኣመታት ደጋፊዎቹን በቅፅበት ኣነቃነቀ፡፡ የተቃዋሚዎቹ ደጋፊዎች ብዛት ኣሽቆለቆለ፡፡ ከዛም ኣልፎ የዋሽንግተን ተቃዋሚዎች የተቃውሞ ኣጀንዳ የሚቀርጽላቸው የኢትዮጵያ መንግስትራሱ ሆነ፡፡ ለምሳሌ የኣባይ ግድብን እገነባለሁ ብሎ ገንዘብ ለማሰባሰብ ከፍተኛ ባለስልጣኖቹን መላክ፣ የግልገል ጊቤ ግድብን መገንባት፣ የእርሻ መሬቶች እንዲለሙ ለውጭ ኣገር ኢንቨስተሮች መሬት መስጠት፣ የእርዳታና በጎ ኣድራጎት ድርጅቶችን ኣዋጅ ማውጣት…… ኣስፈላጊ ሲሆን ደግሞ (ዋሽንግተን ጭር ካለ) ኣንድ ሁለት ጋዜጠኞችን ወይም የፖለቲካ ድርጅት መሪዎችን ማሰር፡፡ ስለዚህ በኣሁኑ ሰኣት የዋሽንግተን ፖለቲከኞች የተቃውሞ ኣጀንዳ ሙሉ በሙሉ የሚቀረጹት በኢትዮጵያ መንግስት ነው ማለት ይቻላል፡፡

ዛሬ ዛሬ የዋሽንግተን ፖለቲከኞች በፖለቲካ ድርጅት ስም ስብሰባ ሲጠሩ ዝር የሚል ሰው ስለጠፋ ሁለት ዘዴዎችን ዘየዱ፡፡ ኣንደኛው ማንኛውም የሚጠራ ስብሰባና የሚጠየቅ የገንዘብ ድጋፍ “ለኢሳት ቴሌቪዥንና ራድዮ ማጠናከሪያ” በሚል ሰበብ እንዲሆን ተደረገ፡፡ እዚህ ላይ ለተወሰነ ጊዜ ተሳክቶላቸዋል፡፡ ቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ ኣሉባልታ፣ ጥላቻና ኣንዱ ሌላው ላይ እንዲዘምት በመቀስቀስ መንግስትን የሚጥሉ ይመስል እንደ ትልቅ ድል ያወራሉ፡፡ ጣቢያችን በምናምን ሺ የEthioTube ተመልካቾች ተጎበኘ ብለው ሳያፍሩ ሪፖርት ያቀርባሉ፡፡ ለኢሳት ተጨማሪ ብር ሲፈለግ ኣበበ ገላው ኣቶ መለስ ዜናዊን ኣምባገነን ብሎ ስብሰባ ኣዳራሽ ውስጥ ስለተናገረ በጥቂት ሰኣታት ውስጥ በኣበበ ስም የገንዘብ ማሰባሰብ ዘመቻ ማካሄድ (ለዛ ኣላማ ታስቦ ይሆን እንዴ እንደዛ የጮኸው? ሊሆን ይችላል፡፡ ምክንያቱም ሰውየው የኢሳት ተቀጣሪ ነው – ስለዚህ ደሞዙን ነው የሸቀለው ማለት ነው፡፡ ኣለበለዚያ እዛ በመናገሩ የሚመጣው ለውጥ ኣይታየኝም፡፡ ምክንያቱም እዛ ኣዳራሽ ውስጥ የነበሩ መሪዎች ስለ ኢትዮጵያና ስለ ኣቶ መለስ ኣስተዳደር ከሱ በላይ እንደሚያውቁ እርግጠኛ ነኝ – እድሜ ለኤምባሲዎቻቸው)፡፡

ስብሰባ ኣዘጋጅተው የሚመጣላቸው ሰው እየጠፋ ስለሄደ የዘየዱት ሌላው ብልሃት ሰዎች “ህዝቡ እኛጋ መምጣት እምቢ ካለ እኛ ህዝቡ ጋ እንሂድ የሚል ነው፡፡ ለዚህ ትክክለኛው ቦታ ደግሞ የኢትዮጵያውያን ስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን ኣሜሪካ (ESFNA) ሆኖ ተገኘ፡፡ እናም ባለፈው ኣመት ስራቸውን ጀመሩ፡፡

በ 2011 ESFNA ዝግጅቱን ኣትላንታ ላይ ለማካሄድ ሲወጥን የክብር እንግዳችንን እንምረጥ ኣለ፡፡ ብርቱካን ሚደቅሳ ኣሉ የዲሲ ፖለቲከኞቹ፡፡ ኣንዳንዶቹ ደግሞ ዝግጅቱ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የየራሱ የፖለቲካ እምነት ይዞ በኣንድነት የኢትዮጵያ ባህልና ስፖርትን የሚያከብርበትና እርስ በርሱ የሚገናኝበት ስለሆነ ፖለቲከኞችን (ለምሳሌ ብርቱካን ሚደቅሳ፣ በረከት ስምኦን፣ ብርሃኑ ነጋ ፣ልደቱ ኣያሌው፣ ዳውድ ኢብሳ የመሳሰሉ) መጋበዝ የለብንም:: እንደተለመደው ሌሎች ኣርቲስቶችና በተለያዩ ሞያዎች ኣገሪቷን ያገለገሉ ሰዎች እንጋብዝ ኣሉና በዛ መሰረትም ድምጻዊ ማህሙድ ኣህመድ የክብር እንግዳ እንዲሆን ወሰኑ፡፡ በዚህ ውሳኔ ፖለቲከኞቻችን ተናደዱ፣ እንደዉም ኣሉ ESFNAን “ከወያኔ ጋ ንክኪ ኣለው”፣ “የኣላሙዲ ተላላኪ ነው”፣ “ሙሰኛ ነው”፣ “ብር ኣባክኗል”፣ “ኦዲት ተደርጎ ኣያውቅም”…..ወዘተ በማለት ድርጅቱን የማፈራረስ ስራ ጀመሩ፡፡ በተለየዩ ወቅቶች የፖለቲካ ፓርቲና የተለያዩ ጥምረቶችን የማቋቋምና የማፍረስ ልምዳቸው በመጠቀምም “የኢትዮጵያ ቅርስና ውርስ ማህበረሰብ በሰሜን ኣሜሪካ (EHSNA) የሚባል ድርጅት ኣቋቋሙ፡፡ ዝግጅቱን የሚያቀርብበት ጊዜም ከ ESFNA ጋር በተመሳሳይ ጊዜ እንዲሆን ወሰኑ፡፡ ብርቱካንም የዝግጅቱ እንግዳ እንድትሆን ኣደረጉ -ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ፡፡ እንዲህም ኣሉን –

“የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ለዘመናት ስታቀርበውና ስትታገልለት የነበረውን የብርቱካን የክብር እንግዳነት ጉዳይ ይሄው እውነተኛና ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ኣሳክተውታል፡፡ ደስ ብሎናል ደስ ይበላችሁ፡፡ድል ለኛ ሞት ለ ESFNA” ኣሉ፡፡

የወያኔ ነው የተባለው ESFNAም ሃሳቡን ቀይሮ ብርቱካንን ጋበዘ፡፡ እንዲህ ነው ጨዋታ፡፡

“ታሪክ ራሱን ይደግማል” እንደሚባለው ዘንድሮ 2012 ደግሞ ሌላ “የመላ ኢትዮጵያውያን የስፖርት ማኅበር ኣንድ (AESAOne)” የሚባል ድርጅት ተቋቋመ፡፡ ከ EHSNA ልምድ በመውሰድም ዝግጅታቸውን ከ ESFNA ጋር በተመሳሳይ ጊዜ (July 1-7) ዋሽንግተን ዲሲ እንዲሆን ኣደረጉ፡፡

በዳላስ እየተካሄደ ያለው የESFNA ዝግጅት ላይ እንደተለመደው ኣዲስ ድርጅት/ጥምረት “የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት” የሚባል በማቋቋም፣ የፖለቲካ ውይይቶችን በማካሄድ፣ የኣበበ ገላውን የጀግንነት ቲሸርት በመሸጥ ወያኔንና ኣዲሱ የመላ ኢትዮጵያውያን የስፖርት ማኅበርን በማውገዝ … ወዘተ እየተከበረ ነው፡፡ በሌላ በኩል ዋሽንግተን ላይ ኣዲሱ ድርጅት የተለያዩ ጥቁር ኣሜሪካዊ ራፐሮችን ጋብዞ ተሳታፊዎቹን ለማዝናናት ሞክሯል፡፡ ፖለቲካዊ ነክ ጉዳዮችን ኣላቀርብም – ነጻ ነኝም እያለ ነው፡፡ ስለዛ ግን እርግጠኛ ኣይደለሁም፡፡

በሁለቱም ድርጅቶች መካከል ከፍተኛ የሆነ ተሳታፊን የማሰባሰብ ፉክክር ተካሂዷል፡፡ በርግጥ በወራት ውስጥ ተቋቁሞ ዝግጅቱን በትልቁ RFK ስታዲየም እያቀረበ ያለው AESAONE 29 ኣመት ያህል ከቆየው ኣንጋፋው ESFNA ጋር ተቀራራቢ የተሳታፊ ቁጥር ያገኛል ብሎ መጠበቅ ኣይቻልም- እና የኣዲሱ ድርጅት የተሳታፊ ቁጥር ቢያንስ ኣያስደንቅም፡፡ በርግጠኝነት መናገር የሚቻለው ግን ነባሩ ESFNA የከዚህ ቀደም ያህል ተሳታፊ እንደማያገኝ ነው፡፡

ሁለቱም ድርጅቶች (ዳላስና ዋሽንግተን) ሲውለበለቡ የታዩት ባንዴራዎች ኣንዱም ቢሆን የዛሬይቷን ኢትዮጵያ ኣይወክሉም፡፡ ይሄም የዲሲ ፖለቲከኞቻችን ምን ያህል ከኢትዮጵያ ህዝብ ወደ ኋላ እንደቀሩ ማሳያ ነው፡፡ ዲሲ RFK ስታዲየም የተውለበለበው ልሙጥ ኣረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሲሆን ዳላስ ላይ ደግሞ ቢያንስ ሶስት ኣይነት ባንዲራ ታይተዋል፡፡ ልሙጡ ኣረንጓዴ ቢጫ ቀይ፣ የወታደራዊ ደርግ ኣርማ ያለውና የዘውዱ ባለ ኣንበሳ ባንዲራዎች ተውለብልበዋል፡፡

የዲሲ ፖለቲከኞች ESFNA ዳላስ ላይ የሚያቀርበውን ዝግጅት ከማስተዋወቅና ከመሳተፍ ይልቅ AESAOne የሚያደርገውን ብዙ ብር ወጥቶበታል ተብሎ የተነገረለት ዝግጅት ማደናቀፍና “ፀረ- AESAONE ሰላማዊ ሰልፍ” ማዘጋጀት ላይ ተጠምዷል፡፡ ስታዲየም ኣካባቢ በመገኘትም ተሳታፊዎቹን ሲሳደቡና ዝግጅቱን ለማደናቀፍ ሲሞክሩ ታይተዋል፡፡ በተቃውሞው ስም ብር ኣሰባስበዋል፣ ዌብሳይትም ከፍተዋል፡፡ በዝግጅቱ ስራዎቻቸውን የሚያቀርቡ ባለሙያዎች ላይም ዘምተዋል፡፡ ኣቤት ተኣምር ተፈጥሮ እነዚህ ሰዎች ስልጣን ቢይዙ ምን ኣይነት የወጣለት ኣምባገነን ስርኣት እንደሚፈጥሩ ሳስበው የኢትዮጵያ ኣምላክ ያለምክንያት እያንገላታቸው እንዳልሆነ እገነዘባለሁ፡፡

በርግጥ ቀድሞውኑም ESFNA ሁሉም ኢትዮጵያውያንን ያሳትፍ ኣልነበረም፡፡ የማይሳተፉ ብዙ ኢትዮጵያን ኣሉ በተለያዩ ምክንያቶች ስለተገፉ፡፡ ለምሳሌ ኣብዛኞቹ ኦሮሞዎች የራሳቸው ዝግጅት ላይ ነው የሚሄዱት፡፡ ለESFNA የኔነት ስሜት የላቸውም፡፡ ዘንድሮ ደግሞ እነዚህ የዋሽንግተን ፖለቲከኞች …. ዋሽንግተን የሚሄደው ትግሬ ብቻ ነው እያሉ ሰብከዋል (ሁሌ የውድቀታቸው መጀመርያ እዛ ላይ ነው)፡፡ በሌላ ኣነጋገር ትግራውያን ዳላስ እንዲሳተፉ ኣልተፈለገም ማለት ነው፡፡ ሆኖም ግን ብዙ ትግራውያን ሁለቱም ቦታ ላይ ታይተዋል፡፡ ዳላስ ላይ የመገኘታቸው ጉዳይ ግን የፖለቲከኞቹ ቀሽት ሳይቆርጥ ኣይቀርም – ኣይፈልጉትማ፡፡

በሁለት ኣመት ውስጥ ESFNA ሶስት የተለያዩ ድርጅቶች ሆኗል (ESFNA, EHSNA, AESAOne)፡፡ በሚቀጥሉት ኣመታት ESFNA እየፈራረሰ ከዚህ በፊት እንደነበሩ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ጥምረቶች ተፈረካክሶ ይሟሟ ይሆን? የሚለው ጥያቄ ጥሩ ጥያቄ ነው፡፡ በርግጥ ኣሁን ያለው ኣካሄድ በትክክል ወደዛ የሚያመራ ነው ሆኖም እድሜ ሰጥቶን ለማየት በትግስት እንጠብቅ፡፡ ዞሮ ዞሮ ግን ከ 20 ኣመት በኋላ እነዚህ ተቃዋሚዎች በኢህኣዴግ 2 ለ 0 እየተመሩ ነው፡፡ ጨዋታውም ሙሉ በሙሉ በራሳቸው በተቃዋሚዎቹ ሜዳ ላይ ሆኗል …. ጨዋታው እየቀጠለ ነው፡፡

ክብር ለኢትዮጵና ለህዝቦቿ !

****************

he author Jossy Romanat can be reached at jossyromanat@gmail.com. You may find other articles by Jossy Romanat here.

One Response to “የዲሲ(DC) ፖለቲከኞች የኋልዮሽ ጉዞ ታሪክ በጨረፍታ”

 1. AKLILU BIZEN said

  we ethiopians does’t matter how every one has out look,we don’t care where from and who U R ,only we concern that our internal capacity building rathen than external forces so as to enssure our dev’t and resonanes!!! with out bais U tried to give information ,I appreciat U ,please keep it up,I am on UR side!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: