Ethio Tribune

Plural News and Analysis on Ethiopia and HOA

 • RSS google news

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS Capital

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS Unknown Feed

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS Unknown Feed

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS Walta

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS DireTube Video

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • Enter your email address to receive notifications of new posts

  Join 481 other followers

 • Meta

 • Articles

 • ምስለ መለስ፡ የማንነቱ ገፅታ

  ምስለ መለስ፡ የማንነቱ ገፅታ

 • Live streaming

 • ETV live streaming
 • RSS Sudan Tribune

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS East Africa News

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS BBC News

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS Aljazeera

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS Climate Change News

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • RSS Technology News

  • An error has occurred; the feed is probably down. Try again later.
 • Archives

 • Flickr Photos: Ethiopia

የአማረ አረጋዊ ጀልባ

Posted by Ethio Tribune on June 9, 2012

የአማረ አረጋዊ ጀልባ ስለ ቀድሞ ወዳጄ ስለ አማረ አረጋዊ አንዳንድ ወጎችን ከየአቅጣጫው እሰማለሁ። ከሰማሁዋቸው ሁሉ ልቤን የሰቀለው ጉዳይ መፅሃፍ ፅፎ መጨረሱን ማወቄ ነበር። ፅፎ ከጨረሰ ሁለት አመት አልፎታል። ይዞት ቁጭ ብሎአል። ስሜቱ ይገባኛል። መፅሃፍ እንደ ጋዜጣ አይደለም። ጋዜጣ ጀልባ ነው። መቅዘፊያ የሌለው ጀልባ ነው። የትም አይደርስም። ጋዜጣ ነፋስ ነው። መፅሃፍ ግን እንደ አክሱም ሃውልት ብርቱ የድንጋይ ምሰሶ ነው። ብዙ የማውቃቸው ሰዎች መፅሃፍ ፅፈው ሲያበቁ፣ ልክ እንደ አማረ አረጋዊ ቆልፈውበት ቁጭ ብለዋል።

እርግጥ ነው፣ ጋዜጣ በባህርይው ነፋስ ነው። የሪፖርተር ጋዜጣ ርእስ አንቀፆች የሚፃፉት በአብዛኛው በአማረ አረጋዊ በራሱ እንደሆነ አውቃለሁ። እለታዊ ናቸው። ኮብላይ እንደ ጥላ ናቸው። በአሉ ግርማ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ በርካታ ርእስ አንቀፆችን ፅፎአል። ዛሬ የትም የሉም።  የወያኔ ተቃዋሚዎች የአማረን ጋዜጣ ያነባሉ። እያነበቡት ግን አያምኑትም። “ዞሮ ዞሮ አማረ ትግሬ ነው” ይሉታል። “ዞሮ ዞሮ አማረ ወያኔ ነበር” ይሉታል። ምክንያታዊ መሆን የሚፈልጉ ደግሞ፣ “ህወሃት ስህተቱን አርሞ እንዲጠናከር እንጂ ስርአቱ እንዲለወጥ አይፈልግም” ሲሉ ይተቹታል።  ወያኔዎች በበኩላቸው የአማረን ጋዜጣ እየተከታተሉ ያነባሉ። እያነበቡትም ግን አያምኑትም። “በርግጥ አማረ የኛ ነበር” ይላሉ። “ቢሆንም ግን ስለእኛ ጎጂ ነገሮችን ይፅፋል።

ለታሪካዊ ጠላቶቻችን አሳልፎ ይሰጠናል።” እና ዞሮ ዞሮ እነርሱም አማረን ከጠላት ጎራ ያስቀምጡታል። እዚህ ላይ አማረ የገና ዳቦ መሆኑን ልብ ማለት ይቻላል።  በረከትና ሼክ መሃመድ የአማረ ቀንደኛ ጠላቶች ስለመሆናቸው ተብሎ ተብሎ የሰለቸ ነው። የኢትዮጵያ የፀጥታው መስሪያ ቤት በበኩሉ አማረን በተመለከተ መካከሉ ላይ ቁማር የሚቆምር ይመስላል። ለአብነት አማረ አረጋዊ ከዳሸን ቢራ ጋር በተያያዘ ተከሶ፣ ታስሮ ወደ ጎንደር ተወስዶ ነበር። በነጋታው ወይም በሶስተኛው ቀን ግን በመከላከያ ሄሊኮፕተር ወደ አዲስአበባ እንዲመለስ ተደርጎአል። እዚህ ላይ የህወሃትን ስሜት በቅርብ እገነዘባለሁ። ርግጥ ነው፣ የህወሃት አመራር የአማረ ደጋፊ ሊሆን አይችልም። ብአዴን ወይም በረከት አሊያም ሼክ መሃመድ አማረ ላይ ያላግጡ ዘንድ ግን አይፈቅዱም። ህወሃት የህወሃትን ሰው ሊያስርና ሊገድል ይችላል። ሌሎች ግን ህወሃትን ይነኩ ዘንድ አይዋጥላቸውም። አማረን ባይወዱትም እንኳ፣ የሌሎችን ድፍረት አይፈልጉትም።  አማረ አረጋዊ አገሪቱን ጥሎ እንዲኮበልል ከፍተኛ ግፊት እንደሚደረግበት ግን ይሰማል።

አማረ ግን ስደትን በህልሙም የሚያስበው አይነት አይመስልም። እልህ ውስጥ መግባቱ ይነገራል። ያውቃቸዋል። ያውቁታል። ከመለስ ጋር የሚተዋወቁት ዊንጌት አብረው ሲማሩ ጀምሮ ነበር። በመቀጠል ሁለቱም የህወሃት አባል ሆኑ። አማረ አረጋዊ ከለንደን ከተመለሰ በሁዋላ፣ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ባለስልጣን መስሪያ ቤት ተቀጥሮ እየሰራ የህወሃትን ሴል ያደራጅ ነበር። የደርግ ነጭ ለባሾች ይዘው አሰሩት። ሁለቱን የአይኖቹን መሸፈኛ ቆዳዎች በስቴፕለር እያጣበቁ በማሰቃየት ምስጢር እንዲያወጣ ሞከሩ። ሊያምንላቸው ስላልቻለ፣ ለቀቁት። አማረ ከእስር እንደወጣ በቀጥታ ወደ አስመራ በረረ። ከአስመራ በሻእቢያ የስለላ መስመር በኩል ወደ ሻእቢያ ነፃመሬት ገባ። ለወራት ያህል ከሻእቢያ ጋር ቆይቶ ወደ ህወሃት ተሻገረ። ከዚያም ከመለስና ከአለምሰገድ ገብረአምላክ ጋር በተቀራራቢ የስልጣን ደረጃ ላይ ሆኖ የፖለቲካ ክፍል ውስጥ ተመደበ። በዚያን ጊዜ በረከት ስምኦን የኢህአፓ ፈዳይን ነበር። አማረ በትግሉ ወቅት በደረጃውም ሆነ፣ በአስተዋፅኦው፣ አሊያም በችሎታው ከበረከት በላቀ እና በራቀ ደረጃ ላይ ነበር። አማረ በማንኛውም መለኪያ ራሱን ከነመለስና ስብሃት ተርታ ያስቀምጣል። እና በዚህ ወቅት በበረከት ግፊት ኢትዮጵያን ለቆ መኮብለል የሞት ሞት ሆኖ ሊታየው ይችላል።  አንዳንድ ጋዜጠኞች “አማረ አረጋዊ አሁንም ከወያኔ ስርአት ጋር ይሰራል” ሲሉ ይፅፋሉ። ሌሎች ደግሞ፣ ‘በቂ ገንዘብና ጠንካራ መንፈስ ስላለው ተቋቁሞአቸው እንጂ፣ እንደማንኛውም የግል ጋዜጣ ተፅእኖ እየተደረገበት ነው። መንግስት ከሰጠው የመኖሪያ ኪራይ ቤት አስወጥተውታል። የግል ቤት ተከራይቶ እንዳይኖርም በተለያየ ዘዴ ያሳድዱታል።

ከዚያም አልፈው የሚስቱ ወላጆች ላይ ጭምር ችግር ፈጥረውበታል’ ሲሉ በተለየ ያዩታል። በዚህም ተባለ በዚያ አማረ ዝምተኛ አይደለም። አከራካሪ እንደሆነ ቆጥሎአል። ይህ ብርቱ ጎኑ ነው።  መቼም አበሻ የሚሰራን ሰው የማውደም ልማድና ጠባይ የተጠናወተው ህብረተሰብ ነው። “ዝም አይነቅዝም” ይልሃል ሲያዳክምህ። “ዝም ያለ አፍ ዝምብ አይገባበትም” የሚል ደግሞ ይጨምርልሃል። “ዝምታ ወርቅ ነው” እያልን ከቀጠልን የአፍራሽ አባባላችን ብዛት ማለቂያ አይኖረውም። ዝምታ ግን ወርቅ አይደለም። በተከፈተ አፍ ዝምብ የሚገባው፣ ሰውየው የእእምሮ በሽተኛ ወይም ጅል ከሆነ ነው። ዝም ማለት ደግሞ ሊነቅዝ ይችላል። መስፍን ወልደማርያም ባመኑበት መንገድ ላይ እየተጓዙ ሩጫቸውን በመፈፀም ላይ ናቸው። ዝምታ ወርቅ እንዳልሆነ እሳቸው ያስተምራሉ። ክርስቶስ ህይወቱ እስክታልፍ ድረስ ዝም አላለም። መስቀሉን ተሸክሞ ሲጓዝ እንኳ፣ ከመናገር አላረፈም። እና ዝምታ ወርቅ ሆኖ አያውቅም። የሚናገሩትን የማውደሙን ልማድ ክርስቶስን ከሰቀሉት ሰዎች የወረሰነው ሳይሆን አይቀርም። አውዳሚ ትችቶችን ፈርተው ዝምታን የመረጡ ሞልተውናል። “ከነገሩ ጦም ይደሩ” ሲሉ ይሰማሉ። መናገርን ሞክረው፣ ደንግጠው የሸሹም ከጥቂት በላይ ናቸው። አማረ ከማይሸሹት መካከል መሆኑ ይታመናል።

ርግጥ ነው፣ በደል እያደረሱበትም አማረ አሁንም ለኢህአዴግ መጠናከር የሚጠቅሙ ርእስ አንቀፆችን በጋዜጣው ላይ ይፅፋል። በመሆኑም አከራካሪ አሳቦችን ማጫሩ አልቀረም። “አማረ ተገለባባጭ ባህርይ አለው” የሚሉ አሉ። አብነት አድርገው የሚጠቅሱት፣ በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት እና በምርጫ 97 ያሳየውን ጠባይ ነው። “የደመራውን አወዳደቅ አይቶ አቋሞቹን አስተካክሎአል” ሲሉ ይተቹታል።  “ሰዎች ያልፋሉ – ተራሮች ግን ይኖራሉ” የሚል የቆየ የአርመኖች አባባል አለ። አማረ አረጋዊ ለአፍሪቃ ቀንድ ህዝብ አስፈላጊ የሆኑ ብዙ ያልተነገሩ ታሪኮችን ያውቃል። በአናቱ የሰላ ብእር ባለቤት ነው። ባላንጣዎቹ ጥቂት አይደሉም። ሰዎች እንደ ጋዜጦች ናቸው። ጋዜጦች ደግሞ እንደ ጀልባ። የት ላይ እንዳነበብኩት ረሳሁት እንጂ፣ “በእውነቱ ሰው ከመቃብር፣ ጋዜጣ ከጀበና ማስቀመጫነት ማምለጥ ይቻለዋልን?” ተብሎ ተፅፎአል። የአማረ መፅሃፍ እንደ በረከት “የሁለት ምርጫዎች ወግ” መዘባበቻ እንደማይሆን ተስፋ አደርጋለሁ።

Tesfaye G/Ab

One Response to “የአማረ አረጋዊ ጀልባ”

 1. shibtam said

  ተስፋዬ አንተ ወራዳ ሻዕቢያ ፣እዚህ እያለህ ያጣሀውን ስልጣን ቅንጅት ወይ ሻእቢያ ይሰጥህ መስሎሃል ii
  ኣንተማ የበለጠ ኣጎብዳጅ ኣልነበርክም ፡፡ እፎይታ እያለህ አለምሰገድ ከተናገረህ በጣም የምትንቀጠቀጥ ለራስህ ለሰራሀው ደመወዝ ይጨመርልን ለማለት ያ የትግራይ ሪፖርተር የነበረው ኪዳነማርያም እባክህ ኪዴ ደመወዝ አንሶብኛል እና ለኣለምሰገድ ንገርልን የምትል አቋመ ቢስ ቡከናም አጭበርባሪ ፡፡ በረከትማ ሁሉን ጉድህን ስንፍናህን አቋመ ቢስነትህ፣አሰመሳነትህ ፣ኣድርባይነትህ ዝክዝከ አድርጎ ስለሚያወቀው የምትሰድበው እና እድሜ ልክህ በረከት በረከት እያልክ ትኖራለህ ፡፡ ኣንተማ እንኳን ኣይደለም የኣማረን ስም ልታነሳ ኣንተ የእፎይታ ተራ ጋዜጣ አምደኛ ነው የነበርከው እሱ በችሎታው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ሃላፊ እያለ ፡፡
  አሁን አንተ የሻዕቢያ ተልእኮህን እየስፈፀምክ ነው ፡፡ ኢትዮጵያን የመበታተን አላማህ ያኔ እናቴን አስመራ ጠይቄ መጣሁ ስትል ነው ከነዶላሩ ያሸከመህ ፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s